የአቤ ቶኩቻው ቀኖና ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ)

Source: http://welkait.com/?p=12433
Print Friendly, PDF & Email

ባለፈው ሰሞን በፌውብርዋሪ 18 ዕለተ ሰንበት በአቻምየለህ እና በአበበ ቶላ (አቤ ቶኩቻው) መካካል ሕብር ራዲዮ ባደረገላቸው “የትግሬ የበላይነት አለ?” ወይስ “የለም?” ስርዓቱ አፓርታይድ ነው ወይስ አይደለም? ወያኔ የትግራይን የበላይነት ለማስቀጠል፤ለማምጣት የተመሰረተ ነው ወይ? ወይስ አይደለም? የሚል ውይይት አካሂደው ነበር። የሕብር ራዲዮ ጋዜጠኛው ሐብታሙ ጥሩ የሆነ የጋዜጠኛነት ችሎታው ባሳየበት በዚህ የውይይት አያያዛዝ (ምንም እንኳ አቤ ቶኵቻው ጣልቃ እየገባ የታምሩን መልስ ብዙ ጊዜ ሥርዓት ባልተከተለ ቢያደናቅፈውም)። ሃብታሙ ስርዓቱ የተመሠረተው በዘር መድልዎና ዘረኛ ነው በሚል አቤን በምሳሌ ለማስረዳት ሲል ምርጫ 97 የተደረገ የመታወቂያ ጉዳይ አስመልክቶ ቢያስረዳውመ አልቀበል ሲለው በዜና የተዘገበው የሁለት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ታሪክ በማንሳት <<‘አንዱ አማራ’ አንዱ ‘አሮሞ’ የሆኑ ተማሪዎች በማስቆም፤ ‘ፌደራል የሆኑት ትግሬ ወታደሮቹ “ሁለቱንም አቁሞው” አንተ ምንድ ነህ? ‘አማራ’፤ አንተስ? ‘ኦሮሞ’ የሚል መልስ ሲያገኙ “አማራውን” ረሸኑት። ለምን ገደልከው ብሎ ከመሃላቸው የነበረው አንድ አብሮአቸው የነበረው የፌደራል አማራ የሆነ ወታደር ትግሬ ወታደሮችን ለምን ገደላችሁት ብሎ ሲቃወማቸው፤ ጠመንጃውን አስወርደው እሱንም ጭምር ገደሉት። ኦሮሞውን ተማሪ “አንተ ግን የጀርባ አጥነታችን ነህ” ብለው ለቀቁኝ ብሎ በሰጠው ጋዜጣዊ ምስክርነት ሰጥቷል። ይህ ስርዓት ምንድ ነው የሚባለው? አንድ ሰው በብሔሩ ምክንያት ተለይቶ ሲገደል ምን ትለዋለህ?>> እያለ ሓበታሙ በዜና የተዘገበውን አሳዛኝ ዜና ለአቤ ቶኵቻው ሊያስረዳው ቢሞክርም “ቀኖናዊ አቁዋም” ስላለው ከሃብታሙም ሆነ ከአቻም የለህ ከሁለቱም ጋር ሊገናኝ አልቻሉም (ስርዐቱን አፓርታይድ ለማለት አስቸግሮታል)።በጣም የሚገርመው ደግሞ ከላይ የተዘገቡት የግድያ ዜና ሰምቼአቸው አላውቀም ይላል። የሚገርመው ይህ የቪዲዮ ምስክርነት በቃለ መጠይቅ የተዘገበው ምስክሩ እራሱ ኦሮሞ ነህ እና “የጀርባ አጥነታችን ነህ” ብለው ሳይገድሉት የለቀቁት ተማሪ ነው። የተዘገበውም እራሱ አቤ ሲሰራበት ከነበረው “ኢሳት” ላይ ተላልፏል። እንዴት ነው ነገሩ! አቤ ቶኩቻው ‘ጭራሽኑ ሰዎች ትግሬው ተጠቃሚ ነው እያሉ ትግሬዎችን ወደ ወያኔዎች እንዲጠጉና እንዲሸሽ እያደረጉት ነው’ የሚል መናኛ እምነቱ እንደመከላከያ አድርጎ ይዞታል። ትግሬዎች መሸሺያቸው ያ ሳይሆን ‘ወያኔን” ከሥልጣን ቦታው ካጣነው አማራ (“ደርግ”) ተመልሶ ሊገዛን ነው የሚል ነው የሚሰጡት ምክንያት (በዓረናው ሊቀመንበር አብርሃ ደስታ ምንጭ መሰረት ደርግ ማለት በትግራይ ሕዝብ እምነት ‘አማራ’ ማለት ነው ብለው የተረጉሙታል ብሎ ነግሮናል)። እንዲያ ሆኖ ግን አቤ ቶኩቻው ለመሸሺያቸው ምክንያት እኛ እንደሆንን ከሳይንስ ትንተና ውጭ የሆነ ሽፋን በመስጠት ተከራክሯል። ….. (Read more, pdf)

Share this post

One thought on “የአቤ ቶኩቻው ቀኖና ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ)

 1. ትግሬ ማለት ማን ነው?
  *በሕወሓት ፕሮግራም መለኪያ መሰረት፡ በአባቱ እና በእናቱ ወይንም በአባቱ ወይንም በእናቱ ትግሬ የሆነ፤
  በትግራዋይነቱ የሚያምን በውጭም ሆነ በውስጥ አገር የሚኖር፤ የትግርኛ ቋንቋውን፤ባህሉን ለማስከበር የሚጥር፤
  የትግራይ ጭቆና የሚሰማው፤ ወዘተ….. ወዘተ… ከሚሉት መለኪያዎች ዋና ዋናዎቹ እነኚህ ናቸው።
  የድርጅቱ መሪ ለመሆንም . ..
  *ሁሉንም ከላይ የተጠቀሱት የትግሬነት ማንነት ትርጉም ያካተተ ሲሆን ከትግሬነቱ በተጨማሪ፤ በድርጅቱ ዕድሜ 3/4ኛ ዕድሜ የኖረ፤ የትግሬነት ስሜት ያለው ፀረ-ፊውዳል-ፀረ ካፒታሊዝም፤ፋሺዝም፤ብሔራዊ ጭቆና የሚታገል
  ዕድሜው ከ21 አመት በላይ፤ ጥብቅ የማያወላውል፤እና ስነ ሥርዓት አክባሪ የሆነ በዚህ መመዘኛ ለድርጅቱ መሪ መወዳደር ይችላል ይላል። እንግዲህ ከላይ ያየናቸው የወያኔ አባልነት መመዘኛ “ትግሬነት” ነው። ትግሬ ያልሆነ ወያኔ ቢሆንም፤ ለድርጅቱ አገልጋይ ለተለየ ጠቀሜታ ተብሎ የተመለመለ ብቻ እንጂ ካልሆነ በስተቀር <> ነው <> ማለት መሆኑን ከዚህ መመዘኛቸው በግልጽ መረዳት ይቻላል።
  ፨ወያኔነትን የፈጠረው።መስራቾቹም ሆኑ መሪዎች እና ተዋጊዎቹ “ትግሬዎች” ካልሆኑ “ወያኔ” ሊመሰርቱ አይቻላቸውምና ። ስለዚህ ወያኔ ማለት ትግሬ ነው። ለዚህም ነው መለያነቱ ትግሬነት ስለሆነ “ሕዝባዊ ወያነ ሓርንት ህዝቢ ትግራይ” የሚል ስም የተሰጠው። ወያኔ ማለት የድርጅት መጠሪያ ነው። ድርጅቱ የተገነባው ደግሞ በትግሬዎች ነው። የግለሰቦች ስበስብ የሆኑ ለአንድ ግብ አብረው ተዋድቀው ወደ ሥልጣን የመጡ ትግሬዎች ናቸው። የተጠቃሚ ብዛት “ሁሉም” ወይንም “ሕዝብ” የሚል ማሰናከያ ውዥምብር እየተገባ የሚደረገው “ሂፒክሪት’ አስመሳይ ክርክር ማቆም አለብን።ድንቁርና ነው። በሕግም በአፈጣጠርም በአንድ ሥርዓት በበለጸጉም ባልበለጸጉት አገሮች “ሁሉም ግለሰብ” (ሕዝብ) እኩል እንዲጠቀም እኩል እንዲደሰት የሚጠብቅ ሰው ካለ በሕልም ዓለም ያለ ብቻ ነው።
  ፨ ሕዝብ የሚባል ልዩ ተደርጎ ግለሰቦችን ከሕዝብ ውጭ እየተደረገ የሚተረጎም ትርጉም “ኮሚኒስታዊ’ ነው። ኮሚኒስቶች በሕብብ/በቡድን/በስብሰብ/ የበላይነት ስለሚያምኑ ግለሰቦች ሲጠቀሙ የነገዱ /የሕዝቡ አባል መሆኑን ይዘነጋሉ። በፍጠረትም በሚዛናዊ ፍርድም ‘ቅድሚያ” የሚሰጠው (ሪኮግኒሽን) ለግለሰብ ነው። ምክንያቱም ሕዝብ የግለሰቦች ስበስብ መጠሪያ ስለሆነ። ግለሰብ ተጠቃሚ ሲሆን የዚያ ማሕበረሰብ ነገድ “ግለሰብ” ተጠቃሚ ነው። ይሰማል?
  ፨ ወያኔ ለመሆን ትግሬነት የግድ ነው።አቤ ቶክቻው ጭራሽኑ ” ሰዎች ትግሬው ተጠቃሚ ነው እያሉ ትግሬዎችን ወደ ወያኔዎች እንዲጠጉና እንዲሸሽ እያደረጉት ነው” የሚል መናኛ እምነቱን እንደመከላከያ አድርጎ ይዞታል። ትግሬዎች መሸሺያቸው ያ ሳይሆን. . .”ወያኔን ከሥልጣን ከቦታው ካጣነው አማራ (“ደርግ”) ተመልሶ ሊገዛን ነው የሚል ነው የሚሰጡት ምክንያት (በዓረናው ሊቀመንበር አብርሃ ደስታ ምንጭ መሰረት ደርግ ማለት በትግራይ ሕዝብ እምነት ‘አማራ’ ማለት ነው ብለው ይተረጉሙታል ብሎ ነግሮናል)።ለተስፋዬ ግብረአባብ ተከላካይን እና አጥቂም ሆኖ ሲፈራገጥ ነበር፡ለሜንጫ አብዮተኛው ጀዋር መሐመድን አግልላችሁ አክራሪና ጽንፈኛ ሆነብን ብሎ ሲያላዝን ነበር!።
  ፨ትግሬ ሆኖ ከድርጅቱ ጋር የሚቃረን አለ፡ ስለዚህም ሁሉም ትግሬተጠቃሚ አይደለም፤የሚል መከራከያ የሚያቀርቡ አሉ። የወያኔ ተቃዋሚ መሆን ትግሬነትህን እንደማይፍቀው ሁሉ፤ ወያኔነት መሆን ትግሬነትህንም ሊፍቀውአይችልም። ስለዚህ ወያኔዎች እንጂ ትግሬዎች ተጠቃሚ አይደሉም የሚለው ክርክር ወያኔ መሆን ትግሬነትህን እንደማይፍቀው
  ሁሉ ተጠቃሚነትህ በትግሬነትህ መሆኑን ስለሆነ ወያኔዎች ትግሬዎች ናቸው እንጂ “ወያኔ” የሚባል ከትግሬዎች ውጭ የሆነ ልዩ “ነገድ” የለም። አራት ነጥብ።
  ፨ ወያኔ ትግሬዎች የገነቡት ድርጅት እንጂ ከሰማይ የወረደ ድርጅት አይደለም። ስለሆነም ወያኔ ማለት የትግሬዎች ድርጅት መጠሪያ ነው። እነ ገብሩ እነ አረጋሽ፤ እነ አብርሃ ደስታ፤ አብርሃ በላይ፤ እኔው እራሴ ጌታቸው ረዳ፤ ገብረመድህን አርአያ…ወዘተ… ወያኔዎች ጋር ቅራኔ ቢኖረንም፤ ትግሬዎች እስከሆንን ድረስና ያችን የትግሬነት “መመዘኛ” እስካሟላን ድረስ፤ በማንኛውም ጊዜ ድርጅቱን ለመቀላቀል የሚያግደን የለም።መመዘኛውን ስለምናሟላ በማንኛውም ጊዜ ጥቅም ለማግኘት ከፈለግን የትግሬነት መመዘኛ ስለምናሟላ ስርዓቱ ተጠቃሚ ከመሆን የሚያግደን
  ነገር የለም። ወሳኙ ወያኔነት ብቻ ሳይሆን ትግሬነት የመጀመሪያው እና ”A must” መመዘኛው ነው። አደለም አንዴ?
  “ዋዛና ቁምነገር በጌታቸው ረዳ ዘብሔረ አክሱም !” ክብረት ይስጥልን።

  Reply

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.