የአቶ ሽመልስ ንግግር የለውጡን አነሳስና የለውጡን ሂደት ለውጡን የሚያይበት አተያይ ትክክል አይደለም ስህተት ነው የሚል ሃሳብ አለኝ

ለውጡ የመጣው በሁሉም ፍላጎትና ተሳትፎ በተለይም ደግሞ በወቅቱ የኦህዲድና የብአዴን አመራሮች ጥምረት እንዲሁም በኦሮሞና አማራ ህዝቦች ትግል በሌሎችም ብሄር ብሄረስብ ህዝቦች ግፊት ነው ። በአጠቃላይ በኢትዮጵያውያን ፍላጎት የኢትዮጵያውያን ጥያቄ ለመመለስ ከለውጡ በፊት የተነሱ አንኳር ጥያቄዎች ለውጡን የግድ ያሉት አንኳር ጥያቄዎች የሁላችንም ጥያቄዎች ስለነበሩ በሁሉም ረገድ ለውጡን የግድ ያሉት መገፋቶች ሁሉንም የገፉ ስለነበሩ ለሁሉም የምትመች ኢትዮጵያን ለመገንባት ቤተኛና አልፎ ሂያጅ የሌለባት ኢትዮጵያን ለመገንባት ፍትሃዊነትን እኩልነትን አላማው ያደረገ ህብረ ብሄራዊ አንድነቷ የተጠበቀ ኢትዮጵያን ለመፍጠር በጋራ ትግል የተደረገበት እንጂ ከየትኛውም ወገን በተናጠል ከፍተኛ ሚዛን የወሰደበት ትግል አልነበረም ። እኩል ርብርብ የተደረገበት የሚናና የቦታ ልዩነት ካልሆነ በስተቀር በመናበብ የመጣ ለውጥ ነው ። በኦሮሚያም የነበረው

Source: Link to the Post

Leave a Reply