የአውሮፓ ህብረት የእስራኤልን የሰፈራ ፈቃድ ውድቅ አደረገ፡፡እስራኤል በወረራ በያዘችው የዌስት ባንክ ዳርቻ አካባቢ ከ3 ሺህ በላይ የሚሆኑ ነዋሪዎቿን ማስጠለል የሚችሉ ቤቶች ግንባታ ማጠና…

የአውሮፓ ህብረት የእስራኤልን የሰፈራ ፈቃድ ውድቅ አደረገ፡፡

እስራኤል በወረራ በያዘችው የዌስት ባንክ ዳርቻ አካባቢ ከ3 ሺህ በላይ የሚሆኑ ነዋሪዎቿን ማስጠለል የሚችሉ ቤቶች ግንባታ ማጠናቀቋን ተክተሎ እና የእስራኤልን ወደ ፍልስጤም የምታደርገውን መስፋፋት ህጋዊ ለመድረግ ሲል ነው ህብረት ስብሰባ የገባው፡፡

በዛሬው እለት የአውረፓ ህብረት እስራኤል ከ1ሺህ በላይ የሚሆኑ ዜጎቼን በፍልስጤም ግዛት ላስፍር ብላ ያቀረበችውን ጥያቄ ውድቅ አድርጎታል፡፡

ህብረቱ ምክንያት ነው ያለውም አካባቢው ሙሉ በሙሉ ደህንነቱ የተጠበቀ ነው ተብሎ ስለማይታመን፤ የእስራኤል ዜጎቿን እዚህ ቦታ ማስፈር በቀጠናው ለሚኖረው ደህንነት እጅግ አስጊ ነው ብሏል፡፡

በመሆኑም ህብረቱ ማንም ያላመነበት እና ያልተስማመበት ቦታ ላይ መኖር ደግሞ አለም አቀፍ ህግንም የሚጻረር ነው ማለታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

እስራኤል ወደ ፍልስጤም የምታደርው ግስጋሴ ለሁለቱ አገራት ግጭት ዋነኛ ሰበብ ይሆናል ብለው በመስጋት፤ እስራኤል ይህንን ድርጊቷን ማቆም አለባት ሲሉ የእንግሊዝ፣ የጀርመን፣ የፈረንሳይ፣ የጣልያን እና የስፔን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አቋማቸውን አሳውቀዋል፡፡

በጅብሪል ሙሀመድ
ጥቅምት 7 ቀን 2013 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply