የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ፖሊስ ቤተክርስቲያናትን በመዳፈር የኢትዮጵያን ባንድራ በማውረድ ላይ ነው

Source: https://mereja.com/amharic/v2/202910

የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ፖሊስ ቤተክርስቲያናትን በመዳፈር የኢትዮጵያን ባንድራ በማውረድ ላይ ነው
ካዛንችስ አዲስ አበባ በሚገኘው በደብረ ፅጌ ቅዱስ ኡራኤል ቤተክርስቲያን የተሰቀለውን ባንዲራ የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ፖሊስ አውርዱ በማለቱ የኡራኤልና የአካባቢው ህዝብ በቆራጥነት አናወርድም የሚመጣውን አብረን እናያለን በማለት መፋጠጣቸውን ለመረጃ ኮም የደረሰው መረጃ ያመላክታል::
Image may contain: one or more people, people standing and outdoor
እንዲሁም አራት ኪሎ በሚገኘው ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን በመግባት ተሰቅሎ የነበረውን የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ፖሊስ ወርሮ በኃይል አውርዶታል።የአፍሪካ ኅብረት ቅዱስ ሚካኤል ወጣቶች የአደባባዩን ሣር ታበላሻላችሁ በሚል ፖሊሥ ሊከለክላቸው ቢሞክርም ወጣቶቹ በሕግ አምላክ እንዳትጠጉን “ የኦነግ ባንዲራ ሲተከል የት ነበራችሁ? ” በሚል ተጨቃጭቀዋል። በኋላም የመከላከያ ፓትሮል የያዙ ወታደሮች መጥተው ፖሊሶቹን ተውአቸው ብለው በማለፋቸው አሁን በወታደሮቹ በመከላከያ ሠራዊቱ ትእዛዝ ወጣቶቹ በሠላም አደባባዩን በኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ በማስዋብ ላይ ይገኛሉ።
Image may contain: one or more people, people standing and outdoorImage may contain: one or more people, people standing and outdoorImage may contain: one or more people and outdoorአራት ኪሎ በሚገኘው ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን
Image may contain: one or more people, sky and outdoorየአፍሪካ ኅብረት ቅዱስ ሚካኤል
 

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.