የአዲስ አበባ ባለቤትነት ጥያቄ በሕግ መነጽር ሲታይ – ባይሳ ዋቅ-ወያ

Source: https://www.zehabesha.com/amharic/archives/94344

ሰሞኑን በተለያዩ መድረኮች የአዲስ አበባን ባለቤትነት በተመለከተ ዜጎች በጎራ ተከፋፍለው ዱላ ቀረሽ የቃላት ጥይቶች ሲለዋወጡ ተስተውሏል። ክርክሩና እንካ ስላንቲያው በመደማመጥና በመከባበር ወይም ከእርስ በርስ ለመማማር፣ ቀድሞ ያልተረዱትን ሃቆች አሁን ተገንዝቦ አቋም ለመቀየር ሳይሆን፣ “የኔ አቋም ብቻ ትክክል ነው” በሚል መሪህ ላይ የተመሠረተ በመሆኑ፣ ይህን ጽንፍ የያዘውን ክርክር፣ ጽንፈኞቹ መሰረት አድርገው የሚከራከሩበትን ”ታሪካዊ ሃቆችንና መረጃዎችን“ ወደ […]

Share this post

3 thoughts on “የአዲስ አበባ ባለቤትነት ጥያቄ በሕግ መነጽር ሲታይ – ባይሳ ዋቅ-ወያ

 1. የኢህአዴግ የወደፊት ዕጣ ፈንታ (ባይሳ ዋቅ-ወያ) may 04, 2008
  የችግሮቹን ቅርጫት ስንከፍተው የሚከተሉትን እናገኛለን፣” ይላሉ ያንቆለጳጰሱትን ሕገመንግስት ሲዘለፉ….ዘጠኝ ክልል አምነው ሁለት የከተማ አስተዳደሮችን ይክዳሉ? ከ14 ክልል ዘጠኝ ሲሆን ቁማሩ(ሙስናው) ያለው እዚያ ላይ ነው።
  ሀ) የብሄር ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ትርጓሜ አጥጋቢ አይደለም። በኔ ግምት፣ ጥራዝ ነጠቅ የሆነው የብሄር ብሄረሰቦችና ሕዝቦች አተረጓጎሙ ነባራዊውን ሁኔታ የሚያንጸባርቅ አልነበረም። በኢትዮጵያ ውስጥ ከ 85 በላይ የተለያየ ቋንቋ ያላቸው ሕዝቦች መኖራቸው እየታወቀ፣ ከነዚህ መካከል በሕዝብ ብዛት ልቀው የሚገኙትን የኦሮሞ የአማራና የትግራይን ህዝብ “ብሄር” ብሎ ራሳቸውን በቻሉ “ክልሎች” ሲመድብ፣ 56 የተለያዩ ህዝቦች የሚኖሩበትን የደቡቡን ያገራችንን ክፍል ግን ባንድ ላይ ጨፍልቆ “የደቡብ ክልል” “ሕዝብ” ማለቱ የብሄር የብሄረሰቦችና የሕዝብ ትርጓሜ የተዛባ አድርጎታል። በህገ መንግሥቱ አንቀጽ 39 ንዑስ አንቀጽ 5 ላይ የሰፈረው ትርጓሜ እንደሚለው ከሆነ፣ ብሄር ብሄረሰብና ሕዝብ ማለት፣
  ሰፋ ያለ የጋራ ጠባይ የሚያንጸባርቅ ባህል ወይም ተመሳሳይ ልምድ ያላቸው፣ ሊግባቡበት የሚችሉበት የጋራ ቋንቋ ያላቸው፣ የጋራ ወይም የተዛመደ ህልውና አለን ብለው የሚያምኑ፣ የሥነ ልቦና አንድነት ያላቸውና ባአብዛኛው በተያያዘ መልክዓ ምድር የሚኖሩ ናቸው በማለት ለሶስቱም አንድ ዓይነት ትርጉም ይሰጣል። ትርጓሜው ሳይንሳዊ ነው አይደለም የሚለውን ወደ ጎን ብንተውና፣ ይህንን የኢህአዴግን ትርጓሜ እንዳለ ብንወስደው፣ ታድያ ሶስቱም አንድ ዓይነት ትርጉም ካላቸውና በመካከላቸው ምንም ዓይነት ልዩነት ከሌለ ወይም ደግሞ ልዩነቱን ማስመር ካልተቻለ፣ ብሄር ብሄረሰብና ሕዝብ ብሎ ለሶስት መክፈሉ ለምን አስፈለገ የሚለውን መሰረታዊ ችግር ይመስለኛል።
  ለ) የኢህአዴግ አወቃቀር ሌላኛው ችግር ነው፣ የኢትዮጵያን የፖሊቲካ፣ የኤኮኖሚና እንዲሁም ሌሎች ተጓዳኝ የህብረተሰቡን ህይወት የሚነኩ ጉዳዮችን የሚወስነው የኢህአዴግ አስፈጻሚ አካል የተዋቀረው ከያንዳንዱ አባል የክልል ድርጅት በተውጣጡ ዘጠኝ (9) ግለሰቦች (በጠቅላላው 36) ሲሆን የማዕከላዊው ኮሚቴ ደግሞ ከያንዳንዱ አባል ድርጅት በተውጣጡ (45) (በጠቅላላው 180) ግለሰቦች ነው። በዚህ፣ ሚዛናዊና ዲሞክራሲያዊ ባልሆነና የህወሃትን አናሳነት ለመሸፈን ብቻ ተብሎ በታቀደው አወቃቀር መሰረት 56 የተለያዩ ህዝቦችን ያቀፈው “የደቡብ ክልል” እና አናሳው የትግራይ ክልልም እኩል አባላት መኖራቸው በራሱ ትልቅ ችግር ይመስለኛል።
  ሐ) ህወሃት፣ ሲፈጠርም ሆነ ዛሬም ዓላማው ትግራይን ከኢትዮጵያ ለመገንጠል ስለሆነ፣ ሌሎቹን የኢትዮጵያ “ዴሞክራቲክ” ድርጅቶችን በኢህአዴግ ሥር ሲያዋቅር፣ ራሱን እንደ ትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር አድርጎ ስለሆነና፣ ከሌሎች “ኢትዮጵያውያን“ ድርጅት ጋር የጋራ ዓላማ ስለሌለው፣ ድርጅቱን (ኢህአዴግን) በህይወት ለማቆየት መሰረታዊ ችግር ያለበት ይመስለኛል። ነጻ አውጪ ድርጅትና የጨቋኙ አገር ድርጅቶችን ባንድ ላይ ለማሰራት መሞከር ውሃና ዘይትን ለማዋሃድ የመሞከር ያህል ነው።
  መ) ኢህአዴግ ሲፈጠር ጀምሮ ጸረ-ህገ መንግሥት ነበር። በፌዴራል ኢትዮጵያ ህገ መንግሥት አንቀጽ 47 ንዑስ አንቀጽ 1 በግልጽ እንደተቀመጠው፣ “የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሬፑብሊክ -ኢፌዲሪ- አባላት ዘጠኝ (9) ክልሎች ናቸው ሲሆኑ አንቀጽ 47 ንዑስ አንቀጽ 4 ደግሞ “የኢፌዲሪ አባላት እኩል መብትና ሥልጣን አላቸው” በማለት ዘጠኙ የኢፌዲሪ አባላት በኢትዮጵያ የፖሊቲካ ሂደት ውስጥ እኩል መሆናቸውን በግልጽ ያስቀምጣል። ይህ እንግዲህ በ1995 ዓም “በህዝቦች ፈቃድ” ሥራ ላይ የዋለውና ዛሬም የህጎቻችን ሁሉ ምሰሶ ሆኖ በማገልገል ላይ ያለው ያገራችንና የመንግሥታችን የፖሊቲካ የኤኮኖሚና ማህበረሰባዊ ትስስር መመርያ የሆነው ህገ መንግሥታችን እንዳካተተው ነው። አንድ ህግ ወይም መመርያ ብቃቱና ተግባራዊነቱ የሚገመገመው በአፈጻፀሙ ላይ ነውና፣ የዚህን የህገ መንግሥታችንን አንቀጽ
  47 ተግባራዊነት ባጭሩም ቢሆን ስንዳስስ ትልቅ ክፍተት እናገኝበታለን። የዛሬ ሃያ ሰባት ዓመት የዛሬውን ቅርጽና ይዘት ይዞ ኢትዮጵያን መምራት የጀመረው ኢህአዴግ ውስጥ በሙሉ አባልነት የታቀፉት ወያኔ የመረጣቸው የአራቱ ድርጅት አባላት ብቻ ነበር። የተቀሩት አምስቱ የፌዴራሉ አካላት ግን “አጋር ድርጅቶች” ተብለው፣ በግንባሩ አመራርም ሆነ ውይይት አንዳችም ተሳታፊነት ሳይኖራቸው፣ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ግን የኢህአዴግን መመርያና ፖሊሲ ያላንዳች ማወላወል እንደራሳቸው ክልል ውሳኔ አድርገው እንዲቀበሉ ተደረገ። የኢትዮጵያ የኤኮኖሚዋም ሆነ የፖሊቲካ፣ አገራዊም ሆነ ዓለም ዓቀፋዊ ግንኙነት መመርያዎችና ፖሊሲዎች የሚቀየሱትና የሚወሰኑት በአራቱ የግንባሩ አባላት ብቻ ሲሆን፣ “አጋር ድርጅቶች” ግን በውይይቱም ሆነ በሚተላለፈው የአፈጻፀም ውሳኔ ላይ አንዳች ተሳትፎ ሳይኖራቸው፣ የግንባሩን ውሳኔ ግን በክልላቸው ውስጥ ሙሉ በሙሉ በተግባር ላይ እንዲያውሉ ተወስኖባቸዋል። የሚገርመው ደግሞ፣ ህገ መንግሥቱ ዘጠኙም የኢፌዲሪ አባላት እኩል መብትና ሥልጣን አላቸው ብሎ በግልጽ እያስቀመጠ፣ በኢህአዴግ አሰራር ግን፣ ከ 85ቱ የኢትዮጵያ ህዝቦች መካከል፣ የሱማሌ የጋምቤላ፣ የጉሙዝና ቤኒሻንጉል፣ የአፋርና የሃረሪ ክልል ዜጎች በምንም ዓይነት የኢትዮጵያ ጠ/ሚር ለመሆን አለመቻላቸው ነው። የኢትዮጵያ ጠ/ሚር ሆኖ የሚያገለግል ሰው መጀመርያ የኢህአዴግ ሊቀመንበር መሆን ስላለበትና የኢህአዴግ ሊቀመንበር ደግሞ የሚመረጠው ከአራቱ የግንባሩ አባል ድርጅቶች ብቻ ስለሆነ፣ “አጋር ድርጅቶቹ”፣ ህገ መንግሥቱን በሚጻረር አሰራር ከጨዋታው ውጭ እንዲሆኑ በመሆኑ፣ኢህአዴግ ሲፈጠር ጀምሮ ህገ ወጥና አምባገነናዊ፣ በዘር መድልዖ መሪህ የሚመራ ድርጅት ነው ብሎ መደምደም ይቻላል።
  **************************************************

  የአዲስ አበባ ባለቤትነት ጥያቄ በሕግ መነጽር ሲታይ – ባይሳ ዋቅ-ወያ
  ” የፌዴራሉም ሆነ የክልሉ ህገ መንግሥት፣ አፈጻጸሙ ላይ ችግር ይኖራቸው እንደው እንጂ ቃልና መንፈሳቸው አሉ ከሚባሉ የሌሎች ዲሞክራት አገሮች ህገ መንግሥት ተርታ የሚያሰልፋቸው ስለሆነ ለውዝግቡ መፍትሄ ይሰጣሉ የሚል እምነት አለኝ።”
  የፌደራሉ ሕገመንግስት
  አንቀጽ 49የፌዴራሉ መንግሥ ርዕሰ ከተማ አዲስ አበባ ነው፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተጠሪነቱ ለፌዴራሉ መንግሥት ይሆናል።
  የኦሮሚያ ህገ መንግሥት፣
  አንቀጽ 6 የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ ከተማ (ፊንፊኔ) አዲስ አበባ ነው።
  (1) አዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልል የምትገኝ ነች…(2)አዲስ አበባ የራሷ አስተዳደር አላት…(3)አዲስ አበባ የፌደራሉ መንግስት መቀመጫ ናት!? ለመሆኑ እነኝህ 6 እስከ 7 ሚሊየን የሆኑ የአዲስ አበባ ሕዝብ ለምን የአፓርታይድ ሥርዓት ተፈረደባቸው? ሕገ ደደቢት አንቀጽ 49/5
  ‘ልዩ ጥቅም’ ህወሓት መለስ ዜናዊ እና ኦነግ ሌንጮ ለታ ሙስና የሰሩበት ሰነድ ነው:: ሙስና እውቅና ያገኘው በሕገመንግስት ተብዬው ነው::
  ሕግ በመነፅር ሳይሆን በልብና አዕምሮ በማነጻጸር የሚሰራ ነው::አራት ነጥብ::
  አቶ አሰፋ ጫቦ “በአሜሪካ ሕገመንግስት ኢትዮጵያን ለመምራት የሚቋምጡ ምሁር ተብዪዎች አሉ” ያሉት ትዝ ይለኛል
  አቶ ባይሳ ዋቆያ ባለፉት ወራት ጽሑፋቸው ኦሮሞ እንደነገሰ ሀገራቸው ገቡ ሰበታ በሚገኘው ቤታቸውን የተከራዩ ግለሰቦች ቀበሌው መብራትና ውሃ እንዳያስገቡ ተከልክለው እሳቸው ሕግ አዋቂና ታዋቂ በሰፈርተኝነታቸው ታዋቂ በመሆናቸው በእየቢሮው ገበተው እንደጮሁና ፍቃድ እንዳሰጧቸው ጻፉ፡ አንዳንድ ስብሰባ ከፊት ወንበር መቀመጣቸው የሕገመንግስት አፍቃሪ እንጂ የሕግ አዋቂ ናቸው ለማለት አያስደፍርም:: ሕገመንግስት ተብዬው ለሁሉም ዜጋ እኩል ካልሰራ የሕግ የበላይነት ቱልቱላ፡ ከላይ የጻፉትም ተቃርኖ እንደተጠበቀ ሆኖ ሌላው ቅጥፈት ህገመንግስቱ በራስ ገዝ ስሜት ለካድሬና ወሮበላ ጉልበት ሆኖ ሁለተኛ መንግስት ሆኖ ሌላውን መጤና ሰፋሪ እያለ ከቤት ንብረት እያፈናቀለ 300መቶ ሺህ የጌድዩ ሕዝብ፡ ከወለጋ የአማራው: ጋሞው ከቡራዩ፡ ጉራጌው ከገለገጣፎ፡ ከሰበታ የኦሮሞ ክልል ውጡ ተብለው ሕጻን አዛውንት አራስ እናትና ልጆች ሜዳ ላይ ተበትኖ እያዩ (ብሔር ብሔረሰብ ቱማታ) ለመሆኑ እንኳን የአዲስ አበባ ልዩ ባለቤትነት ኦሮሚያ የሚባል ካርታና ክልል የት ነበር? አዲስ አበባ የሸዋ ዋና ከተማ አልነበረም? ጭራሽ ከፊንፊኔ ሸገር ይባላል ይህም ፍንፊኔ..ኢንፊን የምትል ውሃ እንደሆነ ሁሉ ሸገርም የራስ መኮንን እና ግንፍሌን ወንዝ የሚሻገሩት የሾላ የቅንብቢት መስኮብ ሰፈር፡ጥሊያንና ፈረንሳይ ለጋሲዎን ሰዎች(አራዶች) የሰየሙት እንጂ ኦሮምኛ አደለም። አዲስ አበባ ከንጉስ ከዳዊት ዘመን ሳንቆጥር ላልፉት 130 ዓመት ብቻ አያት ቅድመ አያቱ ኖሮ፡ ተወልዶ ያደገው፡ወልዶ የከበደው ሳይጨነቅ ከወለጋና ባሌና አርሲ ፉን ፉን ብለው እንዴት ባለቤት ሆኑ? የታሪክ ብረዛና ማጥፋት፡ የመሬት ዝርፊያ፡ የሥም ቅየራው ሳያንስ ኮንደሚኒየም የሚዘርፍ ባለሜንጫ ማነው? በእርግጥ ኦሮሞ አቃፊ ነበር በሜንጫ መጨፍጨፍ ለመቅበር እንጂ ለማቀፍ ነውን?
  “በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ህጋዊ መኖርያ ያላቸውና የክልሉን መሥርያ ቋንቋ የሚችሉ የሌላ ብሄር ተወላጆች ከዞን ከወረዳና ከክልል ባላሥልጣንነት አልፈው በፌዴራል ደረጃ በኦፒዲኦ/ኦዴፓ አባልነታቸው ሚንስትርና ፕሬዚዴንትነት ሆነው ሲሾሙ ባይናችን በብረቱ እያየን ነው።ይለዋል ባይሳ የሕግ ሸውራራ ከጠርሙስ ቂጥ የተሰራ መነጽር ካልሆነ ” የት መቼ እና እንዴት ለመሆኑ ሌሎች በኦሮሚያ ክልል ተብዬው ውክልና አላቸውን!?
  ይህንን ያለ ገደብ መበርጠቅ: መቀደድ: መተርተር: በምን ሕግ ማስቆም ይቻል ይሆን?

  Reply
  1. ሸዋ በሳባ ቋንቋ የጦር ሰራዊት ማለት ነው ይለናል ኘሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ …የቀዳማይ ምኒልክ ሠራዊት ለመጀመሪያ ጊዜ የሰፈረበትም በዚሁ በሸዋ ነው ይለናል ኘሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ።
   ሽዋ በ ኢትዮጵያ ገጸ ምድር መሃል ላይ የሚገኝ ታሪካዊ ሥፍራ ነው። ለብዙ መቶ ዓመታት በሉዐላዊነት በራሱ መሪዎች ሲተዳደር የኖረ የኢትዮጵያ አካል ሲሆን፣ ርዕሰ ከተማው እስከ ፲፰፻፹፱ ዓ/ም በሰሜን ሸዋ ውስጥ በየጊዜው በተለያዩ ሥፍራዎች ሲፈራረቅ ቆይቶ ባለፉት መቶ በላይ ዓመታት ግን አዲስ አበባ ሆናለች። ደብረ ብርሃን ፤
   አንኮበር ፤ አንጾኪያ ፤ ልቼ እና እንጦጦ በተለያዩ ጊዜያት የሸዋ ርዕሰ ከተማዎች ነበሩ። የሸዋ ገጸ ምድር እምብርት ባሁኗ ኢትዮጵያ መሃል የሚገኙት ተራራዎች ናቸው።
   የሸዋ ቀደምት ከተማወች መካከል የአሁኖ አዲስ አበባ በሚኒሊክ ዘመነመንግስት የተመሰረተች ሳትሆን ከዛ በፊት በአፄ ዳዊት የበራራ ከተማ በአሁኗ አዲስ አበባ አካባቢ በተለይም እንጦጦ ላይ የተመሠረተ ሲሆን የኢትዮጵያ መዲናነት ታሪኩ የሚጀምረው በአጼ ዳዊት ዘመነ መንግስት {እኤአ1380-1413} ሲሆን የሚያበቃውም በአህመድ ኢብን ኢብራሂም አል ጋአዚ {በቅጽል ስሙ ግራኝ አህመድ} ጦር በሚቃጠልበት የአጼ ልብነ ድንግል {እኤአ 1508-1540} ዘመን ነው። እኤአ በ1450 ለመጀመሪያ ጊዜ ከተማው ፍራ ማዉሮ የተባለ ቬኒሲያዊ {ጣልያናዊ} ባዘጋጀው የዘመኑ ፈር ቀዳጅ በሆነው የአለም ካርታ ላይም ለመስፈር በቅቷል። ካርታው መሬት ላይ ባሉ መረጃዎች ተመስርቶ የተሰራ ሲሆን እነሱም አዉሮፓ ከነበሩ ኢትዮጵያዉያንና በተለያየ ወቅት በተለይም በአጼ ይስሀቅ {እኤአ 1414-1430} እና አጼ ዘርዓ ያዕቆብ {እኤአ 1434-1468} ዘመን ኢትዮጵያን ከጎበኙ አዉሮፓዉያን የተገኙ ነበሩ። ሰዓሊ ማዉሮም ይህንን አስመልክቶ እንዲህ ይላል፣
   “…{በካርታው ላይ የተመለከቱትን ስለአፍሪካ} ደቡባዊ ክፍሎች ማዉራቴ ለአንዳንዶች አዲስ ነገር ሊሆን ስለሚችል በጥንቶችም {በባለሙያዎች} ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል ስለማይታወቁ ከሰይቶ ጀምሮ ወደላይ ያለውን ጠቅላላ ስዕል ያገኘሁት ከቦታው ተወላጆች ነው ብዬ እመልሳለሁ። እነርሱም ቄሶች ሲሆኑ {በካርታው ላይ ያሉትን} ክፍለ ግዛቶች፣ ከተሞች፣ ወንዞችና ተራሮችን ከነስማቸው በእጃቸው ለእኔ የሳሉልኝ እነርሱ ናቸው።
   ካርታው አሁን ድረስ ያሉ፣ እንዲሁም ስማቸው የማይታወቅ ቦታዎችን የጠቀሰ ሲሆን አቀማመጣቸውንም በመረጃ አስደግፎ ለማሳየት ሞክሯል። ለምሳሌም ከዘረዘራቸው ውስጥ የየረር፣ የዝቋላ፣ የመናገሻና የወጨጫ ተራሮች፣ የዱከምና አዋሽ ወንዞች፣ በወጨጫ ተራራ አካባቢ የሚገኙ የቤተመንግስት ፍርስራሾች፣ ይገኙባቸዋል።”

   ከማዉሮ ካርታ በተጨማሪም በዘመኑ የነበሩ ኢትዮጵያዉያንና የውጭ ሰዎች ስለበራራና አካባቢው ብዙ መረጃዎችን ትተውልን አልፈዋል። አንዳንዶቹን ለመጥቀስ ያህል አሌሳንድሮ ዞርዚ የተባለ የቬኒስ ጣልያናዊ {15ተኛዉና 16ተኛው ክፍለዘመን} ፣ የመናዊው ሺሃብ አድ ዲን {16ተኛው ክፍለዘመን} ፣ እና አዉሮፓ የነበሩ የኢትዮጵያ መነኮሳት፡ አባ ዞርጊ፣ አባ ሩፋኤል፣ አባ ቶማስና አባ እንጦንዮስ {15ተኛዉና 16ተኛዉ ክፍለዘመን} ይገኙበታል። እኤአ በ1529 ሽምብራ ኩሬ {በደብረዘይት ወይም ቢሾፍቱና ሞጆ መሃል ያለ ቦታ} በተደረገ ጦርነት ንጉስ ልብነ ድንግል መሸነፉና ወደሰሜን ማፈግፈጉ ወረብንና የአገሪቱ መዲናን በራራን ለጥቃት ያጋለጠ ሲሆን እኤአ በ1530 ቦታዎቹ በግራኝ አህመድ ጦር ለመያዝ ከተማዋም ለመቃጠል በቅተዋል። እንደሺሃብ አድ ዲን ትረካ ከሆነ የግራኝ ሰራዊት በአስር ቀናት ውስጥ ከአዋሽ ወንዝ መነሻ {የአሁኗ ግንጪ} ተነስቶ በራራ በመድረስ አጭር ቆይታ አድርጓል፣ ከበራራም ሆኖ ግራኝ የተወሰኑ ወታደሮቹን የስድስት ቀን የእግር መንገድ ወደሚፈጀው ደብረ ሊባኖስ ልኮ እንዳቃጠለ ይዘረዝራል። የተቃጠለው የኢትዮጵያ መዲና የነበረው በራራ ከተማ የሚገኝበትን የወረብ ግዛት እንዲያስተዳድር ሙጃሂድ የተባለውን ታማኙን መሾሙንም ይጽፋል።

   ከዚህ ጊዜ አንስቶ እስከ 19ተኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ስለበራራ የሚዘግብ ምንም የጽሁፍ መረጃ አልተገኘም። በ19ተኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ አካባቢ ግን የጥንቱን በራራ ታሪክ የሚያስታዉሱ ግኝቶች መታየት ይጀምራሉ። እኤአ በ1881 በንጉስ ምኒልክ የሚመራው የሸዋ ፣ እኤአ ከ1889 በሁዋላም የኢትዮጵያ መንግስት መዲናውን እንጦጦ ላይ ያደርጋል። እንደዘመኑ ትርክት ከሆነ {ድርሳነ ራጉኤል ላይ እንደተጻፈው} የንጉስ ምንሊክ እንጦጦ ላይ መከተም ከስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ በተጨማሪ ታሪካዊ ትርጉም ነበረዉ፣ እሱም ታሪክ የዘከረዉን የጥንቱን የአጼ ዳዊት ከተማን እንደገና መገንባት፣ ወደአገሪቱ መዲናነትም መመለስ ነበር።

   የግዛቱ ተራራማነት የተፈጥሮ መከላከያ በመሆን ከውጭ ወረራ ለመላ አገሪቱ ደጀን የነበረና በፍትህ የአስተዳደር ዝናውም ለሌላ የኢትዮጵያ ዜጋዎች መጠጊያና መሸሸጊያም ነበር። አንዳንዴም በወራሪ ሕዝቦች ምክንያት ከቀሪው የኢትዮጵያ ግዛቶች ተግንጥሎም አብዛኛው የሰሜን ሸዋ ግዛቶች፣ ማለትም ሰላሌ(ግራሪያ)፤መርሃ ቤ ቴ፤ ደራ፤ መንዝ፤ ተጉለት ፤ ይፋት፤
   ምንጃር እና ቡልጋ ሕዝብ አማራ እና በሂደት የተቀየሩ የሸዋ ኦሮሞዎች ናቸው። በሰሜን ሸዋ ብዙ ታሪካዊ አብያተ ክርሲያናት እና ገዳማት ይገኛሉ። ከነዚህም በዋናነት የሚጠቀሰው፣
   አቡነ ተክለ ኃይማኖት በ ሰላሌ ወረዳ የመሠረቱት ታዋቂው የደብረ ሊባኖስ ገዳም ይገኙበታል።
   #ደብረ_ብርሃን – በ ፲፬፻፵፮ ዓ/ም በ ዓፄ ዘርአ ያዕቆብ የተቆረቆረችውና ስያሜዋን ያገኘችው የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና ከተማ
   አንጎለላ – ከ ደብረ ብርሃን ከተማ በስተ ምዕራብ አሥር ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘውና ሸዋን ከ ፲፰፻፭ ዓ/ም እስከ ፲፰፻፵ ዓ/ም ባስተዳደሩት ንጉሥ ሣህለ ሥላሴ የተመሠረተችው የ ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ የትውልድ ቦታ።
   አንኮበር
   #የቁንዲ_ከተማ – ረጅሙን የዞኑን ተራራ ተንተርሳ የምትገኘው የቁንዲ ከተማ ሌላዋ ታሪካዊ ቦታ ናት። ከተማዋ የተመሰረተችው በመርዕድ አዝማች ወሰን ሰገድ ነው። ከአንኮበር አሥር ኪሎ ሜትር ሲቀር በምትገኘው ቁንዲ የሚገኘው ቤተ መንግሥት በግንብ የተከበበ እንደነበረ በዙሪያው የሚታየው ፍርስራሽ ያረጋግጣል። የ ቁንዲ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ም የዚያን ዘመን የእደ ጥበብ ውጤት ያንፀባርቃል።
   አልዩ አምባ – የአንኮበር ታሪክ ሲዘከር የስምጥ ሸለቆ አካል የሆነችው የአልዩ አምባ ከተማና የአብዱል ረሱል የእስልምና መቃብር ሥፍራ አብረው የሚጠቀሱ ናቸው። አልዩ አምባ ከ አንኮበር ከተማ አሥራ ሁለት ኪሎ ሜትር ያህል ቁልቁል ሲወረድ ትገኛለች። አልዩ አምባ እንደ ሐረር በግንብ የተከበበች ስትሆን በምስራቅ፣ በደቡብና በምዕራብ በሮች አሏት። ከመካከለኛው ዘመን ጀምሮ እስከ ፳ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ድረስ በ ኢትዮጵያ ታሪክ ጥንታዊ ከሚባሉት የቀረጥ ኬላዎችና የንግድ ማዕከል አንደኛዋ ነበረች።(ላኮመንዛ)

   Reply

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.