የአዲስ አበባ ባላደራ ምክርቤት የውጭ ድጋፍ ሰጪ ኮሚቴ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ላይ አገዛዙ ለሚወስደው እርምጃ ኢሳት ሐላፊነቱን እንደሚወስድ አሳወቀ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/174977

ለኢትዬጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት) ቦርድ ፣
ጉዳዩ :- የአዲስ አበባ ባላደራ ምክርቤት ( ባልደራስ) ሰብሳቢ በሆነው የሰብአዊ መብት ተሟጋችና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ላይ አገዛዙ ለሚወስደው እርምጃ ኢሳት ሐላፊነቱን እንደሚወስድ ስለማሳወቅ፣
የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክርቤት (ባልደራስ) ሰብሳቢ የሆነው ጋዜጠኛ እና የሰብአዊ መብት ተሟጋች እስክንድር ነጋ በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢዋ ከሚኖሩ ኢትዬጵያውያን እና ትውልደ ኢትዬጲያውያን ጋር በአገራችን ወቅታዊ ሁኔታ ላይ በኑቬንበር 24/2019 ዓ•ም• ውይይት ማድረጉ የሚታወስ ነው። በውይይቱም ከአገራችን ወቅታዊና አሳሳቢ ሁኔታ እና የቀጣይ የባላደራ ምክርቤቱ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ጋዜጠኛ እስክንድር ከህዝቡ ጋር ምክክር አድርጓል። የጋራ ውሳኔዎችንም አሳርፏል።
የምክር ቤቱ ሰብሳቢ በቨርጂኒያ ሂልተን አሌክሳንድሪያ ያደረገውን ውይይት መሰረት በማድረግ የኢሳት ሳተላይት ቴሌቪዥን “የዲያስፓራ ተቃውሞና ስብሰባ” በሚል ርእስ ሰኞ ቀን “እለታዊ” ፕሮግራም ሰርቷል። በፕሮግራሙም ላይ ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና፣ ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን እና ወንድማገኝ ጋሹ የተሳተፉበት ነበር። እንደ እውነቱ ከሆነ በእለቱ የተሰራው ዝግጅት የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክርቤት የውጭ ድጋፍ ሰጪ ኮሚቴውን እጅግ ያሳዘነ ሆኖ አግኝተነዋል።
የባልደራሱ ምክርቤት ከሰጠን ተልእኮ መካከል ተቋሙን ስም የሚያጐድፉ ተግባራት ተፈጽመው ሲገኙ መከላከል እና ህጋዊ ምላሽ የመስጠት ሃላፊነት ነው። በመሆኑም ኢሳት ከላይ በተጠቀሰው ቀን ያቀረበው ዘገባ እጅግ በጣም አደገኛ እና የሰብሳቢያችንን ህይወት አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑን ባደረግነው ስብሰባ መግባባት ላይ ደርሰናል።
በመሆኑም እነዚህ አደገኛ ሁኔታዎች እና የኢሳት አመራር ቦርድ እንዲወስድልን የሚገቡ እርምጃዎች እንደሚከተለው ቀርበዋል።
፩: ኢሳት የህዝብ ውሳኔን ክዷል፣
በኑቬንበር 24/2019

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.