የአዲስ አበባ ከተማ ላይ ወያኔ የፈጠረው ውዥንብር ላይ የተሰጠ የመፍትሄ ሃሳብ (በኃይሉ ኡርጌሳ)

Source: http://www.mereja.com/amharic/542994

ግብዓተ መሬቱ እጅግ የተቃረበው ወያኔ ሥልጣን ላይ ለመቆየት ከሚጠቀምባቸው መሰሪ ድርጊቶቹ አንዱ የሆነውን በቅርቡ ይፋ አድርጓል። ይኽውም ኢትዮጵያውያን በሙሉ ከመላው የአገሪቱ ማዕዘናት የሚኖሩባትን አዲስ አበባ ከተማን “ልዩ ጥቅም” በሚል ስም ለኦሮሞ ብሔረሰብ አባላት ብቻ ሰጥቻለሁ በማለት እስከ ሶስትና አራት ትወልድ በከተማው የኖሩትን ዜጎች መብት ለመግፈፍና ለማበጣበጥ የጎነጎነውን ሸርና በዚህም ምክንያት ከሚፈጠረው ውዥንብር ተጠቃሚ ለመሆንና በህዝብ መካከል ደም ለማቃባት በመዶለት ላይ ስላለው ሴራ በርካታ አስተያየቶች በመሰጠት ላይ ናቸው። በዚህም መሠረት አቶ ኃይሉ ኡርጌሳ አውስትራሊያ ውስጥ በሚሰራጨው SBS የአማርኛ መርኃ ግብር ላይ “መለያየትን ሳይሆን አብሮ የጋራ ብሔራዊ መግባባት ላይ መድረስ አለብን” በሚል መሪ ሃሳብ ላይ ተመርኩዘው የሰጡትን በሳል ትንተናና አስተያየት አቅርበንላችኋል።

Share this post

One thought on “የአዲስ አበባ ከተማ ላይ ወያኔ የፈጠረው ውዥንብር ላይ የተሰጠ የመፍትሄ ሃሳብ (በኃይሉ ኡርጌሳ)

 1. “እግዝሐብሔር ይባርክህ! እጅህን ቁርጥማት አይንካው! ቀናውን ይግጠምህ!
  ለመሆኑ what Ethiopia? which Ethiopia ? የሚለው በያን አሶባ ይህንን ሰምቷል? ዶ/ር አብርሃም ዓለሙና አቶ ገለታው ዘለቀ ለነበራቸው ትዕግስትና ቀናዊ አመለካከት ይመሰገናሉ ዶ/ር በያን አሶባ ግን ‘አልበሰላችሁም የበለጠ ውይይት ያስፈለጋል’ ሲል ከሚመጥናቸው ሰው ጋር ባለመቅረባቸው በጣም ያሳዝናል ያሳፍራልም። ለነገሩ በኦሮሞ እርጎና ጨጨብሳ ያደጉና በሚሽነሪ የፋፋና የወተት ዱቄት ያደገ እኩል ነው። ለመሆኑ ጃዋር መሐመድ፡ ጸጋዬ አራርሳ..እስቃኤል ጋቢሳና ሌሎች የፖለቲካ ተንታኝና በታኞች፡ ከኃይሉ ኡርጌሳ እኩል ኦሮሞ ናቸውን? ይህ ዘመን ይህ ትውልድ ምን እንደሚፈለግ ገበቷቸዋል? ወይንስ አፍርሰው! አቃጥለው! አጥፋው! በሜንጫ አንገቱን ማለት! ለኦሮሞ ድሃ ገበሬ ዘላቂ ምግብ ነው ብለው የህወሓት መጠቀሚያ፡ ሥልጣንና ሀብት ጠባቂ ሆነው “የልዩ ጥቅማጥቅመኛ” ሙሰኛ/ጎቦኛ ሆነው፡ የኦሮሞን ሕዝብ ክፉ፡ ሰው በላ፡ ጠባብ አድርገው እያቀረቡ ዙሪያውን ጠላት እያፈሩለት ፈረንጅ ሀገር ተደላደለው እየኖሩ፡ በእየ ሥብሰብ አዳራሹ በአማራና ላይ ሲደነፉ ሀገር እንበትናለን! ‘የማያዳግም እርምጃ’በሌላው ዘርና ጎሳ ይወሰድ! እያሉ ዘር ማፅዳትን ሀገር ማፈርስን እንደቋሚ ቅጥረኝነት ተክነውበታል።
  …የልዩ ጥቅም አዋጅ…ህወሓት ቡድን ለኦሮሞ ሕዝብ ልግስና (እረብየለሽ!)
  …ችግሩ ከሕጉ ሳይሆን ሕጉን ከወለደው የዘር አስተሳሰብ ነው።
  … ይህ የዘር ትንተና አማራዎች ከተለያዩ ክልልና ዞኖች ከኖሩበት አፈናቀሏል!…ትግሬዎች በዘራችን ማንነት መኖር ሥለፈራን የሕግ ከለላ ይደረግልን እንዲሉ ተገደዋል!።
  …ቦረና ተወልዶ በሱዳን አሜሪካ ሜኒሶታ የሰፈረ አዲስ አበባን አይቷት የማያወቅ ኦሮሞ በአዲስ አበባ ልዩ ጥቅም ሲኖረው አዲስ አበባ አያት ቅድመ አያቱ የነበሩና እዚያው የተወለደ ሁለተኛ ዜጋ(መጤ ሰፋሪ) ይሆናል።
  …ሱዳን፡ጂቡቲና ግብጽ ንጹሕ ውሃ በነጻ እየጠጡ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ለገፈርሳና ለገዳዲ ውሃ ለኦሮሚያ ክልል ይክፈሉ ማለት…የሕገመንግስት ብቻ ሳይሆን የአስተሳሰብ ዝቅጠት ነው።
  …ይህ ልዩ ጥቅማጥቅም አስገዳጅ አዋጅ ይሁን ሲባል አንቀጽ ፴፱ ኝን ተግባሪዊ እንዲሆን ከመቋመጥ እንጂ አብሮ መኖርን የሚያስብ ለወንበርና ጠረጴዛ አይጨነቅም፡ አብሮ ቤት ለመገንባት ለማደስና ለማስፋፋት እንጂ!?
  ሁላችንም የሀገሪቱ ዜጎች እኩልነት፡ ነጻነት፡ መለያየትን ሳይሆን አብሮ መኖርን ልናራምድ ዜጋው የመሬት ባለቤት ሲሆን የሀገር ባለቤትነት ስሜት ይኖረዋል፡ ላይፈናቀልና ቤተሰቡ እንዳይበተን ዘላቂ ካሳ እንዲያገኝ የሕግ ከለላ ሊኖረው ይገባል።
  ይህ የጫካው ማኒፌስቶ የከተማው ሕገመንግስት ጥቅማጥቅመኛ…ሲል
  ** የአዲስ አበባን ተወላጅ ከምንም ሳይቆጥር(መጤና ሰፋሪ)ሲያሰኝ፡ ጭራሽም በአዲሱ መስተፋቅር በኦሮሚያ ከልላዊ መንግስት..በአዲስ አበባ መስተዳድር..በፌደራሉ መንግስት ተጠርንፈዋል ይላቸዋል።
  ** በረጅም ዘመን የአብሮ መኖር ከሁለት ነገድ የተወለዱና የወለዱ ዜጎችን ምንም የሕግ ዕውቅናና ከለላ ሳይሰጥ ወፍ ዘራሽ ያደረገ ሥርዓት ነው።
  ** በማናቸውም ዘመንና መንግስት ይሁን፡ በድፍን ኢትዮጵያ ተዘዋወሮ የመኖርና የመሥራት ንብረት ማፍራት የማይገሰስ የዜግነት መብት ሆኖ በሌሎች ሰፈር(ክልሌ) የተገኙ ጸጉረ ልውጥ፡ በቁመናቸው፡በአነጋገራቸው ዘይቤ፡ አለባበስና አመጋገባቸው፡ በግንባራቸው ላይ ብጥ፡በቅንድባቸው ላይ ጭረት፡ አካላዊ ጥቃት፡ የንብረት መውደም ዘረፋና የዘር ጭፍጨፋን የጋበዘ ልዩነትን ያራገበ ሥርዓት…” የተዛቡ ግንኙነቶችን ለማስቀረት” በሚል ጥናታዊ የጥፋት ተልዕኮ የጋራ ባሕላዊና ሃይማኖታዊ እሴቶችን በደቦ ያጠፋ በራሱ ሕዝብና ወገን በቀል አመጽና መጠፋፋትን የዘረጋ የወሮበላ ቡድን…ሰዶ ማሳደድ ሲያምርህ ሀገርህን በክልል ለውጥ” በአዳራሽና ሚዲያ ላይ የበቀል ቁርሾ የ፻፴ ዓመት ትርክት እየነፋህ፡ ሕዝብህን የበይ ተመልካችና የኮንደሚኒየም ተመጽዋች ልዩ ጥቅማጥቅመኛ ከማድረግ የበለጠ የብሔር የጎጥ የነገድ አምዕልኮ ሌላ ወራዳ ፖለቲካ ከየት ይገኛል!?። እየተስተዋለ! በቸር ይግጠመን ከምሥጋና ጋር።

  Reply

Post Comment