የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ለጌዴኦ ተፈናቃዮች የ30 ሚሊየን ብር ድጋፍ ለማድረግ ወሰነ

Source: https://fanabc.com/2019/03/%E1%8B%A8%E1%8A%A0%E1%8B%B2%E1%88%B5-%E1%8A%A0%E1%89%A0%E1%89%A3-%E1%8A%A8%E1%89%B0%E1%88%9B-%E1%8A%A0%E1%88%B5%E1%89%B0%E1%8B%B3%E1%8B%B0%E1%88%AD-%E1%8A%AB%E1%89%A2%E1%8A%94-%E1%88%88%E1%8C%8C/

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ለጌዴኦ ተፈናቃዮች የ30 ሚሊየን ብር ድጋፍ ለማድረግ ወስኗል።

ከዚህም በተጨማሪ የከተማዋን ነዋሪ በማስተባበር የቁሳቁስ እና ሌሎች ዕርዳታዎችን የሚያሰባስብ ኮሚቴ በከተማ አስተዳደሩ ማዋቀሩን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኮሚቴውም ከከተማዋ ነዋሪ የሚሰበስበውን ቁሳቁስ በመያዝ በዚህ ሳምንት በቦታው በመገኘት ድጋፍ የሚያደርግ ይሆናል።

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.