የአገሪቱን ኢኮኖሚ አረጋግቶ ለመምራት አልቻለም የተባለው ብሔራዊ ባንክ ዳግም እንዲዋቀር የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ጠየቁ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/152230

Reporter Amharic

ልማት ባንክ የተበላሸ ብድር ክምችት ታቅፎ 16 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ ብድር ማስፈቀዱ ተተቸ
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ባለሙያዎች ማኅበር በጠራው ስብሰባ ላይ የተሳተፉ የኢኮኖሚ ምሁራን፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሚከተላቸው የቁጥጥር አሠራሮችና የባለሙዎቹ አቅም የአገሪቱን ኢኮኖሚ አረጋግቶ ለመምራት አላስቻሉም በማለት ትችት አቅርበው፣ ባንኩ ዳግመኛ መዋቀር እንደሚያስፈልገው ጠይቀዋል፡፡
የኢኮኖሚክስ ማኅበሩ በዚህ ዓመት ለሁለተኛ ጊዜ ባዘጋጀውና ‹‹የፋይናንስ ተቋማት ወቅታዊ ቁመናና ለውጥን የመቋቋም ብቃት›› በሚል ርዕስ በተካሄደው ውይይት፣ የመድረኩ አጋፋሪና ሰብሳቢ በመሆን የመሩት ከፍተኛ የማክሮ ኢኮኖሚ ባለሙያው ኢዮብ ተስፋዬ (ዶ/ር) ናቸው፡፡ የፋይናንስ ተቋማት ከሁለት አሥርታት በላይ ለአገሪቱ ኢኮኖሚያዊ ልማት ወሳኝ ድርሻ መጫወታቸውን ባለሙያው አስገንዝበው፣ ይሁንና አገሪቱ በተገበረቻቸው ሰፋፊ ፕሮጀክቶች ላይ የዋለው ገንዘብና ያስገኘው ውጤት ብሎም በተቆጣጣሪ ባንኩ አቅም ውስንነት የተፈጠሩ ችግሮች ባንኩን መፈተሽ እንደሚያስፈልግ የሚጠቁሙ ስለመሆናቸው አብራርተዋል፡፡ በዚህም ሳቢያ ባንኩ ካለው አቅም፣ ከሚተገብራቸው ፖሊሲዎችና ከሚመራባቸው አሠራሮች አኳያ ዳግም መዋቀር እንደሚያስፈልገው አሳስበዋል፡፡
በመድረኩ ንግግር ያደረጉት ሌላው ከፍተኛ የኢኮኖሚ ባለሙያውና በዘርፉ አንጋፋ ልምድና ሰፊ የአካዴሚ ተሞክሮ ያላቸው ገብረ ሕይወት አገባ (ዶ/ር) ናቸው፡፡ የአገሪቱ የፋይናንስ ተቋማት ቁመና፣ ከአገሪቱ የልማት ፍላጎት አኳያና ዘርፉ ምን ይጎድለዋል? ምንስ እያደረገ ነው? የሚሉ ነጥቦች ላይ ማተኮር እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
‹‹ኢትዮጵያና ሕዝቦቿ ዘላቂ፣ ሁሉን አሳታፊና ለሁሉ የሚጠቅም ልማት ይፈልጋሉ፤›› ያሉት ገብረ ሕይወት (ዶ/ር)፣ ‹‹ሁሉም ኢትዮጵያዊ የተሻለ ሕይወት ሊኖረው ይገባል፤›› በማለት ተቋማቱም ለዚህ ዓላማ መሠለፍ እንደሚገባቸው ተናግረዋል፡፡
የቁጠባ ገንዘብ በማሰባሰብ በተደራሽነትና በአካታችነት ላይ በመሥራት ኢኮኖሚው

Share this post

One thought on “የአገሪቱን ኢኮኖሚ አረጋግቶ ለመምራት አልቻለም የተባለው ብሔራዊ ባንክ ዳግም እንዲዋቀር የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ጠየቁ

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.