የአገሪቱ መሰረታዊ ችግር በሰላማዊ ፖለቲካዊ ውድድር አሸንፈው በሚወጡ አማራጮች መፍታት ይገባል- መድረክ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/173555

የኢትዮጵያዊ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ፓርቲ አሁን ያለው የአገሪቱ ፖለቲካዊ ችግሮችን ለመፍታት ብሄራዊ መግባባትና እርቅ መርሆች መከተል እንደሚገባ አስታውቋል።
Image may contain: 3 people, people sitting, table and indoor

ፓርቲው ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቀው የአገሪቱ መሰረታዊ ችግር በሰላማዊ ፖለቲካዊ ውድድር አሸንፈው በሚወጡ አማራጮች መፍታት ይገባል።
የአገሪቱን የዲሞክራሲ ጉዞ በተሳካ ሁኔታ ለመምራት ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ ቢሆንም በአሁኑ ሰአት ገዥዉ ፖርቲ የህግ የበላይነትን አላስከበረም ሲሉ የመድረክ ምክትል ሊቀ-መንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ተናግረዋል።
መድረክ በተያዘው ዓመት ለሚካሔደው ምርጫም በፕሮግራሙ አማካኝነት ተወዳዳሪ ለመሆን ዝግጅት ማድረጉን ገልጿል።
ፖርቲዉ የሚከተላቸዉ መርሆች አገሪቱን ካለችበት አስከፊ ሁኔታ ለመቀየር መድረክ ከምንም ጊዜውም በላይ ይታገላል ተብሏል።
በተለይም ህገ መንግስታዊ እና ዲሞክራሲያዊ ስርአት እንዲጎለብት በአሁኑ ወቅት ያለው ህገ መንግስት ሁሉንም የፖለቲካ ፖርቲዎችና ህዝቡን ባሳተፈ መልኩ ውይይት ተደርጎበት በህዝበ ውሳኔ ጭምር የሚሻሻልበት ሁኔታ እንዲፈጠር ለማድረግ መድረክ ይታገላል ብሏል።
Source – EBC
Image may contain: 2 people, people sitting

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.