የአፋር ህዝብ የህልውና መሰረት የሆኑት የቀንድ ከብቶች በወረርሽኝ እያለቁ ነው።

Source: https://mereja.com/amharic/v2/112076

ትኩረት ብዙ የሚጮህላቸው አክቲቪስት ለሌላቸው የአፋር አርብቶ አደሮች!
ጋዜጠኛ ኤሊያስ መሰረት እንደነገረን ሰሞኑን አፋር ውስጥ እንስሳት እየሞቱ እንደሆነ ሰማሁ እና ጉዳዩ የሚመለከታቸው ዶ/ር መሀመድ ኑር ጋር ደወልኩ። እርሳቸው እንደነገሩኝም ዝናብ ትንሽ መዝነቡን ተከትሎ የሚያቆጠቁጡ መርዛማ ቅጠላትን የበሉ 12 ከብቶች የሞቱ ሲሆን የታመሙት ከዚህ ይበልጣሉ። ይህ የተከሰተው አድሀር እና ኤልውሀ የተባሉ አካባቢዎች ነው።
“ነገር ግን ሌላው የገንዲ በሽታ በተለይ ግመሎች ላይ ጥቃት እያደረሰ ነው። በፊት እየቆየ ይከሰት ነበር አሁን ግን ከአቅም ማነስ ጋር በተያያዘ ተከታታይ ጉዳት እያደረሰ ነው። ከአጎራባች ክልሎች ወደኛ የመጣበት ሁኔታ አለ። እኛ ባለን አቅም ዘመቻ ለማድረግ እየተንቀሳቀስን ነው።”
Image may contain: one or more people, outdoor and nature

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.