የአፋን ኦሮሞ ትምህርት ለድርድር የሚቀርብ አይደለም – አቶ ሽመልስ አብዲሳ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/140221

የአፋን ኦሮሞ ትምህርት ለድርድር የሚቀርብ አይደለም – የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ
ኢዜአ፤  የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአፋን ኦሮሞ ትምህርት ለድርድር የማይቀርብና ለቋንቋው እድገት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያን ስርዓተ ትምህርት አስመልክቶ በትምህርት ሚኒስቴር የተሰጠው መግለጫ የአፋን ኦሮሞን ተጨባጭ ሁኔታ የማይገልጽ መሆኑንና የክልሉ መንግስት በቋንቋ ጉዳይ ላይ የማያወላዳ አቋም እንዳለው ህዝቡ ሊረዳ እንደሚገባም ተናግረዋል።

የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤትን የማስተዳደር፣ የትምህርት ስርዓትን ማዘጋጀት፣ የስምንተኛ ክፍል ፈተና ማዘጋጀትና አርሞ ውጤት መወሰን ለክልል የተሰጠ ስልጣን በመሆኑ በዚህ ላይ ጫና የሚያሳድር ማንም ሊኖር እንደማይገባ ገልጸው እንደ ከዚህ በፊቱ ሁሉ በአፋን ኦሮሞ የሚሰጥ ትምህርት እንደሚቀጥልም ነው ያሳወቁት።
የክልሉ መንግስት የአፋን ኦሮሞ ቋንቋን ለማሳደግ ከዚህ በፊት በቋንቋው ትምህርት በማይሰጥባቸው አካባቢዎች ጭምር መማሪያ እንዲሆን እየሰራ በመሆኑ ሁሉም ድጋፍ ሊያደርግ እንደሚገባም ነው አቶ ሽመልስ የገለጹት።
በተጨማሪም በክልሉ ውስጥ ከክልሉ ስርዓተ ትምህርት ውጪ የሚያስተምሩ የግል ትምህርት ቤቶች ላይም በዚህ ዓመት የማስተካከያ እርምጃ እንደሚወሰድም ተጠቅሷል።

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.