የአፍሪካ የኢንዱስትሪ ሳምንት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

Source: https://fanabc.com/2019/11/%E1%8B%A8%E1%8A%A0%E1%8D%8D%E1%88%AA%E1%8A%AB-%E1%8B%A8%E1%8A%A2%E1%8A%95%E1%8B%B1%E1%88%B5%E1%89%B5%E1%88%AA-%E1%88%B3%E1%88%9D%E1%8A%95%E1%89%B5-%E1%89%A0%E1%8A%A0%E1%8B%B2%E1%88%B5-%E1%8A%A0/

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 8 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ የኢንዱስትሪ ሳምንት በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።

በአፍሪካ ህብረት መሰብሰቢያ አዳራሽ እየተካሄደ ያለው የኢንዱስትሪ ሳምንት ዛሬን ጨምሮ ለአምስት ቀናት ይቆያል።

ሳምንቱ “የአፍሪካ ኢንዱስትሪን ለአህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጠና ማመቻቸት” በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተካሄደ ያለው።

የአፍሪካ ህብረት ሳምንቱን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ በአህጉሪቱ አካታች፣ ፈጣን እና ቀጣይነት ያለው የኢንዱስትሪ እድገት እንዲመጣ፥ የአፍሪካ ሃገራት መሪዎች፣ ዓለም አቀፍ መንግስታት እንዲሁም ተቋማት ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ እንደሚገባ  አሳስቧል።

በኢንዱስትሪ ሳምንቱ ከአህጉሪቱ የተውጣጡ ከ1 ሺህ በላይ ባለሙያዎችና ፖሊሲ አውጭዎች እየተሳተፉ ይገኛል።

ጀማሪዎችን፣ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን ማበረታታ የኢንዱስትሪ ሳምንቱ ትኩረት ነው።

ይህም በአህጉሪቱ አምራች ዘርፉን በማጠናከር በዓለም አቀፉ ገበያ ውስጥ ተወዳደሪ ለመሆን ያግዛል ተብሏል።

ሳምንቱን የኢፌዴሪ ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የንግድና ኢንዱስትሪ፣ ዓለም አቀፉ የንግድ ማዕከል እና የመንግስታቱ ድርጅት የኢንዱስትሪ ልማት ተቋም በጋራ ያዘጋጁት ነው።

የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና በመጭው ሃምሌ ወር ላይ ተግባራዊ መደረግ ይጀምራል።

 

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.