የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በተዋሐደው ፓርቲ ሕገ ደንብ ላይ ተወያይቶ እንዲጸድቅ ለምክር ቤቱ መራ

Source: https://fanabc.com/2019/11/%E1%8B%A8%E1%8A%A2%E1%88%85%E1%8A%A0%E1%8B%B4%E1%8C%8D-%E1%88%B5%E1%88%AB-%E1%8A%A0%E1%88%B5%E1%8D%88%E1%8C%BB%E1%88%9A-%E1%8A%AE%E1%88%9A%E1%89%B4-%E1%89%A0%E1%89%B0%E1%8B%8B%E1%88%90%E1%8B%B0/

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 8፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በተዋሐደው ፓርቲ ሕገ ደንብ ላይ ተወያይቶ እንዲጸድቅ ለኢህአዴግ ምክር ቤት እንዲመራ ወስኗል።

ላለፉት ሶስት ቀናት ሲወያይ የቆየው ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ሦስት መሠረታዊ ጉዳዮችን ማጽደቁ ተገልጿል።

በዚህም የፓርቲውን ውሕደት፣ አሳታፊነትና አካታችነት እና ሁሉንም ማኅበረሰብ ወደፊት የሚያራምደውን የፓርቲውን ፕሮግራም በመወያየት አጽድቋል።

ከዚህ በተጨማሪም ሕገ ደንቡን በማጽደቅ ለምክር ቤቱ እንዲመራ መወሰኑን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የፌስ ቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

አዲሱ “ብልፅግና ፓርቲ” ከአማርኛ በተጨማሪ ሌሎች የስራ ቋንቋዎችን የሚጠቀም መሆኑም ተገልጿል።

ከዚህ ባለፈም ፓርቲው በፕሬዚዳንትና በምክትል ፕሬዚዳንት የሚመራ ይሆናል ነው የተባለው።

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.