የኢሬሳ/ኢሬቻ በዓል ትውፊትና አከባበር (አፈንዲ ሙተቂ )

Source: https://mereja.com/amharic/v2/55837

የኢሬሳ/ኢሬቻ በዓል ትውፊትና አከባበር
ፀሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ

የኢሬቻን በዓል በማስመልከት አንድ ጽሑፍ እናበረክታለን ባልነው መሰረት ይህንን ኢትኖግራፊ ቀመስ ወግ ጀባ ልንላችሁ ነው፡፡ ታዲያ እኛ ባደግንበት አካባቢ በሚነገረው ትውፊት በዓሉ “ኢሬሳ” እየተባለ ስለሚጠራ በዚህ ጽሑፍ ውስጥም “ኢሬሳ” የሚለውን ስም መጠቀሙን መርጠናል፡፡ ወደ ነገራችን ከመግባታችን በፊት በዚህ ጽሑፍ የሚወሱት ጉዳዮች Carcar and the Ittu Oromo በተሰኘው የኢትኖግራፊ ጥናት ውስጥ በሰፊው የሚዳሰሱ በመሆናቸው ጥያቄ ያላችሁ ሰዎች የጥናቱን የመጨረሻ ውጤት እንድትጠባበቁ እጠይቃለሁ፡፡ ምክንያቱም በጽሑፉ ውስጥ ከቀረበው ትረካ በላይ ሄጄ ወደ ዝርዝር ጉዳዮች እንዳልገባ ጥናቱን የማከናውንበት ደንብ ስለሚያግደኝ ነው፡፡
—-
ጽሑፋችንን የተሳሳቱ ምልከታዎችን በማስተካከል እንጀምራለን፡፡
የዋቄፈንና እምነት ተከታይ የሆኑት ኦሮሞዎች በሙሉ የኢሬሳን በዓል ያከብሩታል፡፡ ይሁንና

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.