የኢትዮጲያ ጠ/ሚኒስትር እና ፕረዜዳንት የአውሮፕላን ትኬት መቁረጥ አለባቸው! 

Source: https://ethiothinkthank.com/2018/05/03/both-the-president-and-prime-minister-must-buy-air-ticket/

የእስራኤሉ ፕረዜዳንት “Reuven Rivlin” በኢትዮጲያ ጉብኝት ለማድረግ የመጡት እንደ ማንኛውም ተሳፋሪ በኢትዮጲያ አየር መንገድ ትኬት ቆርጠው ነው፡፡ በአየር መንገዱ ሰራተኞች መስተንግዶም ደስተኛ መሆናቸው ገልፀዋል፡፡ 


በተመሣሣይ የታንዛኒያው ፕረዜዳንት “Magufuli” በኢትዮጲያ አየር መንገድ የኢኮኖሚ ክፍል ትኬት ቆርጠው ተጉዘዋል፡፡ 


በአንፃሩ የእኛ ጠ/ሚኒስትር ግን ኬኒያ እንኳን ለመሄድ አንዱን አውሮፕላን ላይ ለብቻው ይኮናተራል፡፡ 


ባለፈው ሰሞን ዶ/ር አብይ ባለስልጣናት አላስፈላጊ የውጪ ጉዞ ከማድረግ እንዲታቀቡ መመሪያ መስጠታቸው ይታወሳል፡፡ ነገር ግን፣ ራሳቸው አንዱን አውሮፕላን ለብቻቸው ተኮናትረው እየሄዱ ስለ አላስፈላጊ ወጪ መናገር የለባቸውም፡፡ ለውጥ ከራስ ይጀምራል! ጠ/ሚኒስትሩም ሆኑ ፕረዜዳንቱ እንደ ማንኛውም ተሳፋሪ ትኬት ቆርጠው መጏዝ አለባቸው፡፡ ይህ ሲሆን ከስራቸው ተሰግስገው የሚሄዱትን አላስፈላጊ ተጏዦች መቀነስ ይቻላል፡፡ 

መቼም ጠ/ሚ አብይ የእስራኤሉ ፕረዜዳንት “Reuven Rivlin” ወይም ፕ/ት ሙላቱ ከታንዛኒያው ፕረዜዳንት “Magufuli” የበለጠ የደህንነት ስጋት አለባቸው ሊባል አይችልም፡፡ ስለዚህ የኢትዮጲያ ጠ/ሚኒስትር እና ፕረዜዳንት የአውሮፕላን ትኬት መቁረጥ አለባቸው!  

Share this post

One thought on “የኢትዮጲያ ጠ/ሚኒስትር እና ፕረዜዳንት የአውሮፕላን ትኬት መቁረጥ አለባቸው! 

  1. ጎበዝ !!
    መጀመሪያ የቢሊዮኖችን ዝርፊያ እንቆጣጠርና ከዚያ ወደ ሺዎች እንገባለን፣ትእግስት ይኑረን !!

    Reply

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.