የኢትዮጵያ ሕዝብ ንቃ!ማኅበራዊ እሴትህን ጠብቅ፤ “ፖለቲከኛን ያመነ ጉም የዘገነ!” – በገ/ክርስቶስ ዓባይ       

በገ/ክርስቶስ ዓባይ ነሐሴ 25 ቀን 2012 ዓ/ም ፖለቲካ ማለት የሕዝብ አስተዳደር ማለት ነው። እንግዲህ ‘ሕዝብን ማስተዳደር የሚገባን እኛ ነን’ ብለው የተለያዩ አማላይ አስተሳሰቦችን በመያዝ ሰውን የሚሰብኩ ደግሞ ፖለቲከኞች ሲሆኑ፤ እንደዚህ ያሉትን ተመሳሳይ ፍላጎት ያላቸውን ‘ፖለቲከኞች ነን’ ባዮችን በማሰባሰብ በፓርቲ አደራጅቶ የሚመራው ሰው ደግሞ ፖለቲከኛ ይባላል። ቀደም ባሉት ጊዜያት ጄኦግራፊ ያጠና (የሚያጠና)  ሰው በመንግሥታት አንድም ከፍተኛ ሥልጣን ይሰጠዋል፤ አልያም መንግሥትን ይቀናቀናል በሚል እጅግ የሚፈራና ዓይን የሚጣልበት ሰው ነበር። ምክንያቱም የጂኦግራፊ ምሁር የሆነ አንድ ሰው ስለአንድ አገር ጉዳይ አብጠርጥሮ ያውቃልና። የአገሪቱን ቅድመ ታሪክ፤ የድንበር ሁኔታ፤ የሕዝቦችን የቋንቋ፤ አሰፋፈር፤ ባህልና የኑሮ ሁኔታ፤ የአገሪቱን መልክአ ምድርና ካርታ፤ ከአጎራባች አገሮች ጋር ያላትን የድንበርና የወሰን ግንኙነት፤

The post የኢትዮጵያ ሕዝብ ንቃ!ማኅበራዊ እሴትህን ጠብቅ፤ “ፖለቲከኛን ያመነ ጉም የዘገነ!” – በገ/ክርስቶስ ዓባይ        appeared first on ዘ-ሐበሻ Ethiopian Latest News & Point of View 24/7.

Source: Link to the Post

Leave a Reply