የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባወጣው ጨረታ ማጭበርበር ፈጽሟል ሲሉ ተጫራቾች ከሰሱ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/138244

“ጨረታው ተበልቷል”
የፌዴራል የመንግስት ግዥ ኤጀንሲ
“ጨረታው ግልጽ ስለሆነ የጨረታ መመሪያና ማብራሪያ አልሰጥም”
አየር መንገዱ
“ጨረታውን ማሳገድ ይችላሉ”
የፌዴራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ
Image result for bole ethiopian airlines new terminal
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ ለሚያስገነባው ቁጥር ሁለት ተርሚናል ለተለያዩ የንግድ አገልግሎቶች የሚውሉ ክፍሎች ያወጣውን ጨረታ ማጭበርበሩና ጨረታውን መሰረዙ አግባብ ያለመሆኑን ቅሬታ አቅራቢዎች ገለጹ። አየር መንገዱ ‹‹ጨረታውን የሰረዝኩት በተቋሙ መመሪያና አሰራር መሰረት ነው፤ አሰራሬ ግልፅ ስለሆነም ስለጨረታው ማብራሪያም ሆነ የተቋሙን መመሪያ አልሰጥም›› ብሏል። የፌዴራል የመንግስት ግዥ ኤጀንሲ በበኩሉ “ጨረታው ተበልቷል ማለት ይቻላል›› ብሏል።
አየር መንገዱ ባወጣው ጨረታ የተሳተፉና የቴክኒክ መስፈርቱን ያሟሉ ስምንት ቅሬታ አቅራቢዎች ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ ባቀረቡት አቤቱታ ‹‹ተቋሙ ከአገሪቱና ከዓለም አቀፍ ህግ የጨረታ ስርዓት ውጪ ያፈነገጠ አሰራርን ፈፅሞ ስላጭበረበረን ጉዳት አድርሶብናል›› ብለዋል።
እንደ ቅሬታ አቅራቢዎቹ ማብራሪያ የጨረታው የመዝጊያና የመክፈቻ ጊዜ በግልጽ መነገር ሲገባው በሚጠበቀው ሰዓት አልተካሄደም፤ ጨረታውን ለማሸነፍ 40 በመቶ ነጥብ የሚይዘውን ቴክኒካል መወደዳሪያ ነጥብ በጊዜው በጽሁፍ አላሳወቀም፤ 60 በመቶ ነጥብ የሚይዘውን የቀረበውን የገንዘብ መጠን መወዳደሪያ ያሳወቀው ከረጅም ጊዜ በኋላ ነው።
‹‹አየር መንገዱ ጨረታውን ለመክፈት ተጫራቾችን ከጠራ በኋላ ‹ጨረታው ሲከፈት ታያላችሁ እንጂ ተጫራቾች ያቀረቡትን ዋጋ አልገልፅም› በማለቱ፤ ያቀረብነው ዋጋ ካልተገለጸ የእኛ መገኘት ለምን አስፈልገ? እንዲህ አይነት የጨረታ አካሄድ ሊኖር አይገባም ብለን በመቃወማችን ጨረታው ሳይከፈት ልንመለስ ችለናል›› ብለዋል።
ቅሬታ አቅራቢዎቹ ‹‹አየር መንገዱ ጨረታውን በድጋሚ ለመክፈት ጠርቶን ‹ጨረታው ሲቀደድ ታያላችሁ እንጂ የመወዳደሪያ ዋጋውን አንነግራችሁም፤ በጽሁፍ እናሳውቃችኋለን› ብሎ አሰናብቶናል፤ በጽሁፍ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.