የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም በቢዝነስና ኢንተርፕሬነርሺፕ ዘርፍ በተፅዕኖ ፈጣሪነት ሽልማት ተበረከተላቸው

Source: https://fanabc.com/2019/02/%E1%8B%A8%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE%E1%8C%B5%E1%8B%AB-%E1%8A%A0%E1%8B%A8%E1%88%AD-%E1%88%98%E1%8A%95%E1%8C%88%E1%8B%B5-%E1%8B%8B%E1%8A%93-%E1%88%B5%E1%88%AB-%E1%8A%A0%E1%88%B5%E1%8D%88%E1%8D%83/

አዲስ አበባ፣የካቲት 4፣2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም በቢዝነስና ኢንተርፕሬነርሺፕ ዘርፍ በተፅዕኖ ፈጣሪነት ሽልማት ተበረከተላቸው ።

ሽልማቱን ያበረከተላቸውም በአፍሪካ በልዩ ልዩ ዘርፎች ታላላቅ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች የሚሸልመው ኤም. አይ ፒ.ኤ.ዲ. አዋርድ የተሠኘው ድርጅት መሆኑ ነው የተገለፀው።

በዚህ መሰረትም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ በቢዝነስና ኢንተርፕሬነርሺፕ ዘርፍ በተፅዕኖ ፈጣሪነት መሸለማቸውን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ያገኘኘው መረጃ ያመላክታል።

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.