የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ከፍተኛ ሹመኞች ከመንግስት ደሕንነቶች ጋር ተመሳጥረው 68 ሚሊዮን ብር መዝብረዋል ተባለ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/111566

68 ሚሊዮን ብር ምንድን ነው?? ( ምንሊክ ሳልሳዊ )
68 ሚሊዮን ብር ከሦስት የሐጅ ጉዞዎች ብቻ የመጅሊሱ ሠራተኞች ሳይኾኑ በልዑካን ቡድን ስም በመጅሊሱ ወጪ ወደ ሐጅ በሄዱ ሰዎች ምክንያት ብቻ ከመጅሊሱ የተመዘበረው የገንዘብ መጠን ነው፡፡ በ2008 ዓ.ል 17 ሚሊዮን 514 ሺህ፣ በ2009 ዓ.ል 29 ሚሊዮን 82 ሺህ እንዲሁም በ2010 የሐጅ ወቅት 11 ሚሊዮን 161 ሺህ 200 ብር፤ በጥቅሉ 68 ሚሊዮን 918 ሺህ 400 ብር፡፡ ይኼ ገንዘብ በአንድ ዘርፍ ብቻ የተመዘበረ ነው፡፡ በአውሮፕላን ትኬት፣ በሆቴልና ማረፊያ ኪራይ፣ በምግብ ግዢና በመሳሰሉ ዘርፎች የሚመዘበረው አጠቃላይ የገንዘብ መጠን ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ ነው፡፡
የሐጅና ዑምራ ጉዞን የሚያስተናብረው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት (መጅሊስ) ከፍተኛ ሹመኞችና አንድ አንድ የመንግሥት ሲቪልና የጸጥታ ኋላፊዎች በሐጅ ጉዞና ሂደቱ ላይ ከፍተኛ የጥቅም ትስስር በመፍጠር በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር የገንዘብ ምዘበራ ይፈጽማሉ፡፡ ይህ የተቀናጀ የዘረፋ ድርጊት እንዲቆምና በድርጊቱ የተሳተፉ የመጅሊስ ሹመኞች ለፍርድ እንዲቀርቡ በተደጋጋሚ ሙስሊሙ ማኅበረሰብ ሲጠይቅ ቆይቷል፡፡ ከመንግሥትና ከሚመለከታቸው አካላት ግን በቂ ምላሽ አልተገኘም፡፡
ይኼንን የሕዝብ ጥያቄ ዳግም ለመንግሥትና ለሚመለከታቸው አካላት ለማቅረብና፣ በመጅሊስ የሐጅ ጉዞ ሒደት ውስጥ ብቻ የሚፈጸሙ እጅግ ከፍተኛ ደረጃ የደረሱ የሙስና ወንጀሎችና በደሎችን የሚያጋልጥ የማኅበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ይደረጋል፡፡ ዘንድሮም ልንዘረፋ? በሚል መሪ ቃል የሚካኼደው ዘመቻ ከነገ ረቡእ ሚያዚያ 16 እስከ ጁሙዓ ሚያዚያ 18 ለሦስት ቀናት የሚቆይ ነው፡፡ በዘመቻው በሰነድ የተደገፉ የገንዘብ ዘረፋዎች፣ ክሕግ አግባብ ውጪ የሚፈጸሙ የሀብት

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.