የኢትዮጵያ እና የኬንያ ህዝቦች ለሰላም እንዲሰሩ ጥሪ ቀረበ

Source: https://fanabc.com/2019/11/%E1%8B%A8%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE%E1%8C%B5%E1%8B%AB-%E1%8A%A5%E1%8A%93-%E1%8B%A8%E1%8A%AC%E1%8A%95%E1%8B%AB-%E1%88%85%E1%8B%9D%E1%89%A6%E1%89%BD-%E1%88%88%E1%88%B0%E1%88%8B%E1%88%9D-%E1%8A%A5/

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 15 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኬንያ ምክትል ፕሬዚዳንት ዊልያም ሳሙኤል ሩቶ በኢትዮ – ኬንያ የጋራ ድንበር አካባቢ የሚኖሩ የገብራ፣ ቦረና እና እንዲሁም በሌሎች አዋሳኝ የድንበር አካባቢዎች የሚኖሩ ህዝቦች ለሰላም እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።

ምክትል ፕሬዚዳንቱ የኬንያ የገብራ ማህበረሰብ የሙያተኞች ማህበር ባዘጋጀው የባህል ፌስቲቫል ላይ ባደረጉት ንግግር በድንበር አካባቢ ባሉ በእነዚህ ህዝቦች መካከል ያለው የማህበረሰብ ልዩነት ከግጭት ይልቅ የትብብር ምክንያት መሆን አለበት።

በኬንያ የኢፌዴሪ አምባሳደር መለስ ዓለም በበኩላቸው በመንግስታት መካከል ያለውን ወዳጅነት ዘላቂ ለማድረግ ግጭቶችን ለማስወገድ እና ሠላምን ለመገንባት የባህል ዲፕሎማሲን መጠቀም አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።

በፌስቲቫሉ ላይ የኢትዮጵያ የባህል ቡድን የተለያዩ ትዕይንትና ውዝዋዜዎችን ያቀረበ ሲሆን፥ የኢትዮ – ኬንያ የህዝብ ለህዝብ ዲፕሎማሲ እንዲጠናከር በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ እያደረገ ላለው ጥረት ምስጋና አቅርዋል።

የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከዚህ ቀደም የቦረና እና የቱርካና ፌስቲቫሎች ላይ ተሳትፎ ማድረጉን በኬንያ ከኢፌዴሪ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.