የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ስርዓት ልየታ መመሪያ በዛሬው እለት ይፋ ተደረገ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 7 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በዚህ መሰረት ተቋማቱን…

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ስርዓት ልየታ መመሪያ በዛሬው እለት ይፋ ተደረገ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 7 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በዚህ መሰረት ተቋማቱን በአምስት የትኩረት መስኮች የተለዩ ሲሆን፥ በዚህም የምርምር፣ አጠቃላይ፣ የአፕላይድ ሳይንስ፣ የሳይንስና ቴክኖሎጂ እና የቴክኒካል ዩኒቨርስቲዎች ተብለው ተለይተዋል። በምርምር ዩኒቨርስቲነተ የተመደቡ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትም፥ አዲስ አበባ፣ አርባ ምንጭ፣ ባህርዳር፣ ጎንደር፣ ሀረማያ፣ ሀዋሳ፣ ጅማ እና መቐለ ናቸው። አክሱም፣ አምቦ፣ አርሲ፣ አሶሳ፣ ደብረ ብርሃን፣ ደብረ ማርቆስ፣ ዲላ፣ ድሬዳዋ፣ ጅግጅጋ፣ ኮተቤ፣ ሰመራ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ወልቂጤ፣ ወለጋ እና ወሎ ዩኒቨርስቲ የአፕላይድ ዩኒቨርስቲዎች ተብለዋል። አዲግራት፣ ቦንጋ፣ ቦረና፣ ቡሌ ሆራ፣ ደባርቅ፣ ደብረ ታቦር፣ ድምቢ ዶሎ፣ ጋምቤላ፣ እንጅባራ፣ ጂንካ፣ ቀብሪ ደሃር፣ መዳ ወላቡ፣ መቅደላ አምባ፣ መቱ፣ ሚዛን ቴፒ፣ ኦዳ ቡልቱም፣ ራያ፣ ሰላሌ፣ ዋቸሞ፣ ወራቤ እና ወልዲያ ዩኒቨትስቲዎች ደግሞ አጠቃላይ ዩኒቨርስቲዎች ሆነዋል። የአዳማ ሳይንስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ እና የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች ደግሞ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲነት ተለይተዋል። በቴክኒካል ዩኒቨርስቲ ስር ደግሞ የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተመድቧል። ይህንን ውሳኔ ለማሳለፍ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ የሌሎች ሀገራትን ተሞክሮ መሰረት በማድረግ ጥናቱ ስለመደረጉም ተነስቷል።ይህንንም የልየታ ምክረ ሃሳብ ተግባራዊ ለማድረግ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት በማድረግ እንደሆንም ተጠቁሟል። ዘገባው የኤፍቢሲ ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply