የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ-ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) በስራ አስፈጻሚነት የመረጣቸውን 21 አባላት ይፋ አደረገ፡፡

Source: https://mereja.com/amharic/v2/119098

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ-ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) በስራ አስፈጻሚነት የመረጣቸውን 21 አባላት ይፋ አደረገ፡፡

አባላቱ ብቃትን፣ ትምህርትን፣ ለፓርቲው ሊሰጡ የሚችሉትን ጊዜ እና የፓርቲውን ዓላማ በትክክል መረዳታቸውን ታሳቢ በማድረግ ተመርጠዋል ብሏል፡፡
ኢዜማ በምርጫ ተወዳድረው ለማሸነፍ ያላቸው ቁርጠኝነትና ይቅር ባይነታቸው ከግምት ውስጥ መግባቱንም ነው በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ያስታወቀው፡፡
ስራ አስፈጻሚ አባላቱን የመምረጡ ስራ ጊዜ ተሰጥቶት ከፓርቲው መስራች ጉባዔ ጀምሮ መካሄዱንም አስታውቋል፡፡
ፓርቲው አዲስ የካቢኔ አወቃቀር ስልትን በመከተል የመንግስትና የፓርቲ ስራ ተለይቶ መከናወኑም ገልጿል፡፡
በምርጫው መሰረትም በመንግስት ትይዩ ሆኖ በተዋቀረው የስራ አስፈጻሚ ስብስብ ውስጥ የፓርቲውን መሪና ምክትል መሪ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋን እና አቶ አንዷለም አራጌን ጨምሮ ሌሎች 7 የፓርቲው ሰዎች በአባልነት መካተታቸው ይፋ ሆኗል፡፡
የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ እና ምክትላቸው ዶ/ር ጫኔ ከበደ እንዲሁም የድርጅት ጉዳይ ሃላፊው አቶ ዋሲሁን ተስፋዬ በተካተቱበት የፓርቲው የዕለት ተዕለት ስራ አስፈጻሚ ዝርዝር ውስጥ ደግሞ በበጀትና ፋይናንስ፣ በህዝብ ግንኙነት፣ በሴቶችና ወጣቶች፣ በሙያ ማህበራትና በዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፎች ሌሎች 14 የፓርቲው አባላት ተካተዋል፡፡
ፓርቲውንና ህዝብን በቅንነት ለማገልገልና ሃላፊነታችንን በታማኝነት ለመወጣት ዝግጁ ነን ያሉት ስራ አስፈጻሚ አባላቱ ቃለ መሃላም ፈጽመዋል፡፡

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.