የኢትዮጵያ የባህል ቡድን ወደ ኤርትራ ያቀናል

Source: https://fanabc.com/2019/12/%E1%8B%A8%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE%E1%8C%B5%E1%8B%AB-%E1%8B%A8%E1%89%A3%E1%88%85%E1%88%8D-%E1%89%A1%E1%8B%B5%E1%8A%95-%E1%8B%88%E1%8B%B0-%E1%8A%A4%E1%88%AD%E1%89%B5%E1%88%AB-%E1%8B%AB%E1%89%80/

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 3 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢፌዴሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ብዙነሽ መሰረት የሚመራው እና ከ60 በላይ አባላትን የያዘው የልዑካን ቡድን ወደ ኤርትራ ሊያቀና ነው።

ልዑኩ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ ከብሔራዊ ቲያትር፣ ከታዋቂ ደምጻውያንና የጃኖ ባንድ ሙዚቀኞችን ያካተተ ከ60 በላይ አባላትን የያዘ ነው።

የባህል በድኑ ጉዞ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ የተፈጠረውን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ያለመ ነው።

ቡድኑ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ሲሆን የሙዚቃ ዝግጅት ለማቅረብ ከመጭው ሰኞ  ጀምሮ ወደ ኤርትራ ይጓዛል።

የባህል ቡድኑ በቆይታው በአስመራ፣ ከረን እና ምጽዋ ከተሞች የተለያዩ የሙዚቃ ዝግጅቶችን እንደሚያቀርብ ይጠበቃል።

የኤርትራ የባህል ቡድን ባለፈው ዓመት የካቲት ወር ላይ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ተመሳሳይ ዝግጅቱን በአዲስ አበባ፣ ባህር ዳር እና ሀዋሳ ከተሞች ማቅረቡን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

 

 

 

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.