የኢትዮጵያ ፖሊስ ተቋምና አገልግሎትን ማዘመን የሚያስችል የሪፎርም ስራ ተጀመረ

Source: https://fanabc.com/2019/08/%E1%8B%A8%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE%E1%8C%B5%E1%8B%AB-%E1%8D%96%E1%88%8A%E1%88%B5-%E1%89%B0%E1%89%8B%E1%88%9D%E1%8A%93-%E1%8A%A0%E1%8C%88%E1%88%8D%E1%8C%8D%E1%88%8E%E1%89%B5%E1%8A%95-%E1%88%9B/

አዲስ አበባ፣ነሃሴ 16፣2011 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፖሊስ ተቋምና አገልግሎትን ፕሮፌሽናልና ዘመናዊ ለማድረግ የሪፎርም ስራ ተጀምሯል።

የሪፎርም ጥናት ቡድኑ የፖሊስ ተቋምና አገልግሎት ያለበትን ሁኔታ ዳሰሳ በማድረግ በጥንካሬ እና በክፍተት የሚታዩትን ለመፍታት የሚያስችል ምክረ ሀሳብ አቅርቧል።

በውይይቱ ላይ የሰላም ሚኒስቴርና የፌዴራል ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈውበታል።

በዚህ ምክረ ሀሳብ መሰረት የህግና ፖሊሲ ጉዳዮች፣ የሰው ሀብት ልማትና አስተዳደር ጉዳዮች፣ ተቋማዊ ግንኙነትና አደረጃጀቶች ለማዘመን የሚሰራ መሆኑ ተገልጿል።

እንዲሁም የሎጅስቲክስና የቴክኖሎጂ አቅርቦትና አጠቃቀምን ደረጃቻቸውን የጠበቁ ለማድረግ መታቀዱን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ እንዳሉት ፥የፖሊስ ተቋምና አገልግሎትን ሪፎርም ማድረግ ለሀገራችን ወቅታዊና አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።

በተዘጋጀው ሰነድ ላይም በቀጣይ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር ተከታታይ የውይይት መድረኮች በማካሄድ በህግ፣ መመሪያና ደንቦች ላይ ማሻሻያዎች እንደሚደረጉ አስታውቀዋል።

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.