የኢንዶኔዥያው ከፍተኛ የደህንነት ሚኒስትር የስለት ጥቃት ተፈጸመባቸው

Source: https://fanabc.com/2019/10/%E1%8B%A8%E1%8A%A2%E1%8A%95%E1%8B%B6%E1%8A%94%E1%8B%A5%E1%8B%AB%E1%8B%8D-%E1%8A%A8%E1%8D%8D%E1%89%B0%E1%8A%9B-%E1%8B%A8%E1%8B%B0%E1%88%85%E1%8A%95%E1%8A%90%E1%89%B5-%E1%88%9A%E1%8A%92%E1%88%B5/

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የኢንዶኔዥያው ከፍተኛ የደህንነት ሚኒስትር ጀኔራል ዊራንቶ የስለት ጥቃት ተፈጸመባቸው፡፡

የኢንዶኔዥያ የደህንነት ሚኒስትር ጄኔራል ዊራንቶ በባንተን ግዛት ጃቫ ደሴት ፓንደግላግ ከተማ በጉብኝት ላይ በነበሩበት ወቅት በስለት መወጋታቸው ተነግሯል፡፡

አሁን ላይ ሚኒስትሩ ሆስፒታል ገብተው የጤና ክትትል እየተደረገላቸው ነው ተብሏል፡፡

ጥቃቱ በሚኒስትሩ ላይ መፈፀሙን የሃገሪቱ ፖሊስ ማረጋገጡም ነው የተነገረው፡፡

የሀገሪቱ ብሄራዊ ፖሊስ ቃል አቀባይ ደዲ ፕራሰይቶ ጥቃት እድራሹ በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጸዋል፡፡

ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ አንድ የፖሊስ ባልደረባ ላይም ጉዳት ደርሷል ነው ያሉት፡፡

ጄኔራል ዊራንቶ በፕሬዚዳንት ጆኮ ዊዶዶ ልዩ ትዕዛዝ በሀገሪቱ ምዕራባዊ ክፍል ፑፓ ክልል የተቀሰቀሰውን ያለመረጋጋት በበላይነት ሲከታተሉ ነበር ተብሏል፡፡

የቀድሞው ወታዳራዊ መሪ ጀኔራል ዊራንቶ በከፍተኛ የደህንነት ሚኒስትርነት የተሾሙት በአውሮፓዊያኑ 2016 መሆኑን ዘገባው አስታውሷል፡፡

ምንጭ፡- አልጀዚራ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.