የኣባይ ወልዱ ከስልጣኑ መወገድ እና የአዜብ መታገድ በኣስገደ ገብረስላሴ ዓይን

Source: http://www.zehabesha.com/amharic/?p=83263

በተጨማሪ እስከ መጭው የፓርቲው ጉባኤ  ወይዘሮ ኣዜብ መስፍን ታገደች ፣በየነ መኩሩ ከስራ ኣስፈጻሚ ወደ ተራ ማእከላይ ኮሚቴ ወርዶ እንዲቆይ ተደርጓል ። ሌሎችም ኣዲስ ኣለም ባሌማ  በማስጠንቀቅያ ታለፈ ፣ ብርሀነ ኪዳነማርያም (ማራት )  ከስብሰባ ጠፍቶ የት  እንዳለ የማይታወቅ በሌለበት ታግዳል ፣  በርከት ያሉ   ኣማራር ማስጠንቀቅያ  እየተሰጣቸው እንዳለ፣የኣምስት ሳምንትሰብሰባ በድራማ ተዘጋ ። ሂስ ግለሂስ እየቀጠለ እንዳለ ቢታወቅም  […]

Share this post

One thought on “የኣባይ ወልዱ ከስልጣኑ መወገድ እና የአዜብ መታገድ በኣስገደ ገብረስላሴ ዓይን

 1. ** “መለስ ኖረ አልኖረ…ዘር ይሁን ኖረ አልኖረ..ፋጡማ (አዜብ) ኖረች አልኖረች…ህወሓት የብሔር ብሔረሰቦችን ፖለቲካል ኢኮኖሚ በአንድ ወሮ በላ ቡድን ጥላ ሥር አድርጎት ይቀጥላል። ዘመኑ የኢትዮጵያ የከፍታ ነው!? አላሉም ሰዎች እንዲህ ለቀቁ ወጡ፡ ገቡ፡ ፈረጠጡ፡ ተብጠለጠሉ፡አስጠነቀቁ፡ ተጋጩ፡ ተለያዩ፡ ተጋጠሙ አኮረፉ፡ የሚሉ ቱማታ ምንድነው!? ለቀቁ የተባሉትም ከኋላ እንደተደበቁ ታይቷል።

  ** ይህ ሁሉ ጭፈራ የኔን ድንግል ለማስደብደብ ነው? አለች አሉ ኮረዳ? አዳሜ ላንቃው እስኪታይ እልል ሲል እጁ እስኪላጥ ሲያጨበጭብ ታዝባ!

  “እጃችን እስኪሻክር እንሠራለን ያለው ሙሰኛው ነው ኪራይ ሰብሳቢው ነበር?

  *ይህ ሁሉ ደንበር ገተር ሁለት ወር የፈጀ ቱማታ ምንድነው? ጥልቅ ብስባሶ በጥልቅ ታድሶ እያሽኮረመሙ፡ ተደርዳሪና ተደራዳሪ…ኪራይ ሰብሳቢና ተሞሳሟሽ…ደጋፊና ተደጋፊ…አጋርና ተለጣፊ…ተቃዋሚና ተቋቋሚ..ተጧሪና ከዳተኛ፡ ፖለቲከኛና ሜ/ጀ ነጋዴዎች የፅሁፍ ውድድር የት ለመድረስ ይሆን!?

  የኋላዊት እመቤት ከሥራቸው ታገዱ (ለግዜው!?) በቋሚነት የእኔና ተጠቅላዩ ባለቤቴ ጭንቅላት ባይኖር ህወሓት እና ኢፈርት አይኖሩም አላሉም ነበር!?
  “የባለቤቴ ራዕይ ሳይበረዝና ሳይሸራረፍ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር እሰራለሁ” አላሉም? ማን ሸረፈው እና ተሸረፉ? ሙሰኞች እየበሉ እንሱ እንዳይጋለጡ እኔን ያማሉ ያሉትን አሁን እነማን እንደሆኑ ያጋልጣሉ? ወይስ ውሸት ነበር? ሳይተነፍሱ ተቀድመው ተወገዱ?…ለነገሩ የባለቤታቸው ፎቶ ፭፻፵፯ ፓርላማ አባል መኝታ ቤትና ፓርላማ ከተሰቀለ ሁሉም በሳቸው ሙት መንፈስ ከተመራ ፋውንዴሽኑ በተገለባበጠ የቸሮታ ቼክ ከሞላ ምን ይፈለጋሉ!? ማንም ገንዘባቸውን አያገኘውም፡ካገኙት ይውሰዱት አሉ? ‘የዕዝን ቼክ’ ያመጡ ዝርዝር ዶላር በሻንጣ ከአውሮፕላኑ መቀመጫ ሥር ወስደዋል፡ አደለም እንዴ? ዋሸን?
  የአጼ ዮሐንስን ት/ቤት በባላቸው ሥም ያስለወጡ፡ ፫ሺህ፭፻ የመናፈሻ ቦታ በባላቸው ሥም የያዙ፡ ያለ ደመ-ወዝ በፖለቲካ ምትሃት ቤተሰባቸውን የሚያኖሩ ባሕታዊ፡ ለመሆኑ ከእንግዲህ ቢለቁ የትግራይ ሕዝብ ደስ ይለዋል? ይከፋዋል? ሌላውስ ዲሞክራሲያዊ ብሔርተኛ ይጠግባል? ይራባል?
  ** ይልቁንም የይገባኛል ጥያቄ እንደማፋጠን፡ የሰው ሥልጣንና ሀብት በመቁጠር፡ ግዜና ትውልድ አምክኖ እንደማባከን የመሰለ የቁጭ ይበሉ ፖለቲካ አስጠሊታ ነገር የለም። ሰው አባልቷል ሀገር ማስበላቱ አይቀርም። ዋ እየተስተዋለ!

  Reply

Post Comment