የኤርትራን ግዛት በሃይል የተቆጣጠረችው ኢትዮጵያ ለክልሉ ሰላም ጠንቅ ናት ተባለ

Source: http://amharic.abbaymedia.com/archives/36348

አባይ ሚዲያ
በወንድወሰን ተክሉ

የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ምኒስትር የሀገራቸው ሉዓላዊ ግዛት በኢትዮጵያ ቁጥጥር ስር መሆኑ ችግሩ ከኤርትራም አልፎ ለአፍሪካ ቀንድ ሰላም መናጋት ምንጭ ይሆናል ሲሉ በተ.መ.ድ ጎረቤታቸውን ከሰሱ።

አቶ ኦስማን ሳሌህ መሀመድ በተ.መ.ድ 72ኛው የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለጸጥታው ጥበቃ ምክር ቤት ባቀረቡት የሀገራቸውን ሁለት መሰረታዊ ጥያቄዎች ምክር ቤቱ በ2009 ላይ የጣለውን ማእቀብ እንዲያነሳና በተጨማሪም ምክር ቤቱ በጎረቤታቸው ኢትዮጵያ በሃይል ተይዞብኛል ያሉትን ግዛት እንዲያስለቅቅላቸው አበክረው መጠየቃቸውን የአፍሪካን ዜና ገጽ ዘግባል።
ሁለቱ ሀገሮች በ1998 ግንቦት ወር መጀመሪያ በኤርትራ ሃይሎች ባድመን ወራሪነት ቀጥሎም ከ9ወራት በሃላ በኢትዮጵያ ዘመቻ ጸሃይ ግባት ውጊያ በ1999 እና በ2000 ላይ እጅግ ደም አፋሳሽ ጦርነት ያካሄዱ ሲሆን ገልለተኛ ሃይሎች ከሁለቱም በኩል ከ72ሺህ ህዝብ በላይ በጦርነቱ አልቆበታል ሲሉ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ በኩል ግዛቴ በኤርትራ ሃይሎች ተወስዶብኛል በሚል በከፈተችው የመልሶ ማጥቃት ዘመቻዋ አወዛጋቢውን የባድመን ክፍል ጨምሮ 25ኪሎ ሜትር የኤርትራን ግዛት እንደተቆጣጠረች [በምእራብ ኤርትራ እስከ ባሬንቱ ድረስ]በአፍሪካን ሕብረት ሸምጋይነት በአልጂሪያው ፕሬዚዳንት አብዱላዚዝ ቡታፍሊካ አፈራራሚነት የአልጀርሱ ስምምነት ተብሎ የሚጠራውን የሁለቱን ሀገሮች ስምምነት መፈረም ይታወቃል።

በአልጀርሱ ስምምነት መሰረትም ሁለቱ ሀገሮች የተወዛገቡበትን እና ጦር የተማዘዙበትን የድንበር ይገባኛል ጥያቄ ይግባኝ በሌለው ዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ዘ-ሄግ በመሄድ ዳኝነት በመጠየቃቸው ፍርድ ቤቱም የሁለቱን ሀገሮች የይገባኛል ጥያቄና ያቀረቡትን ደጋፊ ማስረጃዎች መሰረት በማድረግ የግጭቱ እምብርት የሆነችውን የባድመን አብዛኛ ክፍል ተገቢነቱን ለኤርትራ በማድረግ መፍረዱም ይታወቃል።

የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ኢትዮጵያ በመርህ ደረጃ እቀበላለሁ ለተፈጻሚነቱ ግን ከአስመራ ጋር ልደራደር ስትል ኤርትራ ደግሞ በበኩላ በፍርድ ቤት ባለቀ ጉዳይ ላይ የምድራደርበት ምክንያት የለም እቀበላለሁ ካልሽ ባድመን አስረክቢኝ በማለት አቃም በመውሰዱ የሁለቱ ሀገሮች የአልጀርሱ ስምምነት ተጥሶ አንደኛው ሌላኛውን መክሰስ፣ማጥቃትና ማስጠቃት በሰፊው ሲቀጣጠል ማስተዋል ተችላል።

የህወሃት መራሹ የኢትዮጵያ መንግስት ከ16በላይ የአስመራውን መንግስት ተቃዋሚ ሃይሎች እውቅና በመስጠት እንዲደረጁና እንዲታገሉ ሲረዳ በአስመራ ያለው የሻእቢያ መንግስትም በሩን ለማንኛእም የኢትዮጵያ መንግስት ተቃዋሚ ሃይል በመክፈት ሲያደራጅና ሲያስታጥቅ ታይተዋል።

ከዚህ ተግባራቸውም ሌላ ሁለቱ ገዢዎች በሱማሊያ ጉዳይ በይገባኛል [ፖለቲካዊ የበላይነት ማለት ነው] የእጅ አዙር ፍትጊያ የአዲስ አበባው ገዢ ሰባት አባላትን ያቀፈው የአፍሪካ ቀንድና ምስራቅ አፍሪካ ሀገራትን ያቀፈው ኢጋድን ድጋፍ በማግኘት ጸረ አስመራ መንግስት ዘመቻውን በማጣጣፍ የአሜሪካን፣የአፍሪካ ሕብረትን እና ብሎም የአውሮፓና የተ.መ.ድ ድርጅቶችን ድጋፍ በማሰባሰብ ኤርትራን እንድትገለል ማድረግ የተቻለው ሲሆን በ2009 ላይ ተ.መ.ድ በኤርትራ ላይ ማእቀብ እንዲጥል መደረጉ የሚዘነጋ አይደለም።

በዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት የተወሰነለትን መሬት [ባድመን ]ለማግኘት ያቃተው የአስመራው መንግስት በአሜሪካና ምእርባዊያን ዘንድ የአሸባሪዎችን ይደግፋል አመለካከታዊ አቃማቸውና በአንጻሩም የህወሃት መራሹ መንግስት በአፍሪካ ቀንድና በክልሉ አሸባሪነትን በመዋጋት ጠንካራ አጋር ተብሎ የዋሽንግተንን እና የምእራባዊያንን ድጋፍና አመለካከት ማግኘት መቻሉ ለአስመራው መንግስት ጥያቄ ፍትሃዊ መልስ ከዓለም አቀፉ ተቃማት በኩል እንዳያገኝ እንዳደረገው ከሂደቱ መረዳት ተችላል።

ይህ የአሁኑ የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ምኒስቴር አቶ ኦስማን ሳሌህ ጥያቄ ኢትዮጵያ የጸጥታውን ምክር ቤት በፕሬዚዳንትነት በምትመራበት ወቅት የቀረበ በመሆኑ ይበልጥ አስቸጋሪ እንዳደረገባቸው ተንታኞች የተናገሩ ሲሆን የኤርትራ ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ፍትሃዊ መልስና ውሳኔ ማጣትና ብሎም ለማግኘት ምቹ ሁኔታ አለመኖር ሀገሪታ በፍርድ ቤቱ የተወሰነላትን የባድመ ግዛት በሃይል ካልሆነ የምታገኝ አይደለችም ሲሉ ዲፕሎማቶች ይናገራሉ።

በኢትዮጵያ በኩል የፍርድ ቤቱ ውሳኔ የባድመን ህዝብ እኩል ለእኩል የሚከፍል በመሆኑ የሚተገበር አይደለም የሚል አቃም በመያዛ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ የመተግበር እድሉ መንምኖ ታይታል።

ሆኖም በኤርትራ በኩል ተስፋ ባለመቁረጥ ተ.መ.ድ በኢትዮጵያ በኩል የተያዘብኝን ግዛቴን ያስለቅቅ የሚለው ጥያቄ በተደጋጋሚ ግዜ ሲቀርብ የተስተዋለ ሲሆን ዘንድሮም በውጭ ጉዳይ ምኒስትራ በኩል አስመራ ለተ.መ.ድ ተመሳሳዩን ጥያቄ ማቅረባን ለማወቅ ሲሆን ምኒስትሩ ለጸጥታው ምክር ቤት ባሰሙት ንግግር “Eritrea calls on the Security Council to ensure the end of this flagrant violation of international law and several UN resolutions,” የዓለም አቀፉን ህግ የመጣስ ሁኔታ ምክር ቤቱ ማስቆም አለበት በማለት ባድመ ላለፉት 15ዓመታት በህገ-ወጥ ሁኔታ በኢትዮጵያ ህዛት ስር መካተታን ገልጸው ድርጊቱ መቆም አለበት ብለዋል።

የኤርትራ ጥያቄ ከተ.መ.ድ አጥጋቢና ፍትሃዊ መልስ ይሰጠዋል ተብሎ ባይጠበቅም ሀገሪቱ ከጎረቤታ ጋር ያለችበትን ሁኔታ በግለጽ የተለየ ምስል ማሳየት ይቻለዋል ይላሉ ተንታኞች።

ህወሃት መራሹ የአዲስ አበባው መንግስት ላለፉት ሁለት ዓመታት በሀገሪቱ ውስጥ የተነሳውን ህዝባዊ ዓመጽ የአስመራው መንግስት እጅ ያለበት ነው እያለ መክሰሱ ይታወቃል።

Share this post

One thought on “የኤርትራን ግዛት በሃይል የተቆጣጠረችው ኢትዮጵያ ለክልሉ ሰላም ጠንቅ ናት ተባለ

Post Comment