የኤርትራው ልዑክ ለመቀበል ዝግጅት ማጠናቀቁን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ

Source: http://www.yegnagudday.com/2018/07/13/%E1%8B%A8%E1%8A%A4%E1%88%AD%E1%89%B5%E1%88%AB%E1%8B%8D-%E1%88%8D%E1%8B%91%E1%8A%AD-%E1%88%88%E1%88%98%E1%89%80%E1%89%A0%E1%88%8D-%E1%8B%9D%E1%8C%8D%E1%8C%85%E1%89%B5-%E1%88%9B%E1%8C%A0%E1%8A%93/

በኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሚመራ የከፍተኛ ባለስልጣናት ልዑክ ነገ አዲስ አበባ የሚገባ መሆኑን ተከትሎ አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቁን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ህዝቡ በሰኔ 16ቱ የአዲስ አበባ ሰልፍ ያሳየውን ጨዋነት ነገም እንዲደግም የጠየቀው ኮሚሽኑ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና ከወጣቶች ጋር በመተባበር አስፈላጊውን ዝግጅት አድርጎ ማጠናቀቁን አስታውቋል፡፡

ከአቀባበል ስነስርዓቱ ጋር በተያያዘ ምንም አይነት የሁከት እና ጸጥታ ችግር እንዳይገጥም ከ1 ሺ በላይ ወጣቶች በጸጥታ ማስከበር ተግባሩ ላይ ይሳተፋሉ ያሉት የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር አቶ ዘይኑ ጀማል እያንዳንዱ ዜጋ ሃላፊነቱን እንዲወጣ እና የሁለቱን ሃገራት ይፋዊ ባንዲራዎች ብቻ እንዲጠቀም ጠይቀዋል።

የባለፈው አጋጣሚ ለአዲሱ አመራር ትምህርት የሰጠ ነው ያሉት አቶ ዘይኑ ህብረተሰቡ ስነ ስርዓቱን ለማበላሸት ፍላጎት ያለው አካል በተመለከተ ጊዜ በአፋጣኝ ለፖሊስ እንዲያሳውቅ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

አጠራጣሪ አዝማሚያዎችን የሚመለከት ማንኛውም አካል በስልክ ቁጥር
09-44-70-37-45
09-12-33-72-00
09-44-05-46-80
09-11-60-80-24
ማሳወቅ እንደሚችልም ኮሚሽነሩ አስታውቀዋል፡፡

The post የኤርትራው ልዑክ ለመቀበል ዝግጅት ማጠናቀቁን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ appeared first on Yegna Gudday.

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.