የእንጦጦ ሐመረ ኖኅ ቅድስት ኪዳነ ምህረት አንድነት ገዳም ሙዚየምን ተመርቆ ተከፈተ

Source: https://fanabc.com/2019/01/%E1%8B%A8%E1%8A%A5%E1%8A%95%E1%8C%A6%E1%8C%A6-%E1%88%90%E1%88%98%E1%88%A8-%E1%8A%96%E1%8A%85-%E1%89%85%E1%8B%B5%E1%88%B5%E1%89%B5-%E1%8A%AA%E1%8B%B3%E1%8A%90-%E1%88%9D%E1%88%85%E1%88%A8%E1%89%B5/

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የእንጦጦ ሐመረ ኖኅ ቅድስት ኪዳነ ምህረት አንድነት ገዳም ሙዚየምን ዛሬ  አስመረቀ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ፥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅርሶችን ጠብቃና ተንከባክባ እዚህ አድርሳለች ብለዋል።

አሁን ያለው ትውልድ ተንከባክቦ የመጠበቅና ለትውልድ የማስተላለፍ ሃላፊነት አለበት ሲሉም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ቅርስና ጥናት ጥበቃ ባለስልጣን ዳሬክተር አቶ ዮናስ ደስታ በበኩላቸው፥ ሙዝየሙን ለማዘመንና ወደ ዲጅታል ላይብረሪ ለማሳደግ በቀጣይ እንደሚሰራ ገልፀዋል።

በሐመረ ኖኅ ሙዚየም ውስጥ የኢትጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የታሪክ ጉዞና የገዳማት ታሪክ በከፊል የሚያሳዩ እንዲሁም በርካታ ንዋየ ቅድሳት፣ መጽሀፍት፣ አልባሳትና የተለያዩ ረጅም እድሜን ያስቆጠሩ መገልገያ ቁሳቁሶች ይገኛሉ።

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.