የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከረር ያለ ተቃውሞ ልታሰማ ነው

የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከረር ያለ ተቃውሞ ልታሰማ ነው

PHOTO- FILE

ዋዜማ ራዲዮ- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በቅርቡ በኦሮሚያ ክልል በተከቷዮቿና በደብሮቿ ላይ አነጣጥሮ የተፈጸመ ነው ያለችውን ጥቃት በተመለከተ ነገ፣ ሐምሌ 20 ቀን፣ መግለጫ ልትሰጥ ነው። መግለጫው ጥቃት የተፈጸመባቸውን አካባቢዎች ተዘዋውሮ በጎበኘው የቤተ ክርስቲያኒቱ ልኡካን ቡድን ቀዳሚ ሪፖርት ላይ የተመሠረተ እንደሚሆን ታውቋል።

ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለዋዜማ እንደገለጹት የልኡካን ቡድኑ አጠቃላይ ግምገማ በመንግሥት ላይ የከረረ ወቀሳና ትችት የሚያንጸባርቅ ነው። ቤተክርስቲያኒቱ ባለፉት ሁለት ዓመታት ስታንጸባርቅ የነበረው ትችት ለዘብ ያለና በአብዛኛው ከባለሥልጣናት ጋራ በሚደረጉ ስብሰባዎች ብቻ የተወሰነ እንደነበር ያስታወሱት የዋዜማ ምንጮች፣ የሰሞኑ ሁኔታ በቤተ ክርስቲያኒቱ መሪዎችና ተከታዮች ዘንድ ከፍተኛ የጥቃትና የቁጭት ስሜት መፍጠሩን ያረጋግጣሉ።

የነገው መግለጫ ይህ ስሜት በመጠኑ የሚገለጽበት እንደሚሆን ዋዜማ ከምንጮቿ ተረድታለች። መግለጫው በቤተክርሲቲያኒቱ ተከታዮችና ተቋማት ላይ የደረሰውን ጉዳትና የመልሶ ማቋቋም ጉዳዮች የሚዳስስ ይሆናል።

ዝርዝሩን ይዘን እንመለሳለን

The post የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከረር ያለ ተቃውሞ ልታሰማ ነው appeared first on Wazemaradio.

Source: Link to the Post

Leave a Reply