የኦሮሚያ ክልል መንግስት የክልሉን ሠላም በማረጋገጥ ሂደት የላቀ ሚና ለተጫወቱ የፀጥታ አካላት የዕውቅና ስነ ስርዓት እያካሄደ ነው

የኦሮሚያ ክልል መንግስት የክልሉን ሠላም በማረጋገጥ ሂደት የላቀ ሚና ለተጫወቱ የፀጥታ አካላት የዕውቅና ስነ ስርዓት እያካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የከልሉን ሠላም በዘላቂነት በማረጋገጥ ሂደት የላቀ ሚና ለነበራቸው የፀጥታ አካላት እውቅና ሰጥቷል ።

የዕውቅና ስነስርዓቱ በአዳማ ገልማ በአባ ገዳ አዳራሽ እየተካሄደ መው የሚገኘው፡፡

በስነስርዓቱ ላይ የኦሮሚያ ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳና የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

የእውቅና ስነ ስርዓቱ የላቀ አፈፃፀም ለነበራቸው ፖሊሶች የማዕረግ እድገት መስጠትን ይጨምራል ተብሏል ።

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ አራርሳ መርዳሳ የክልሉ ፖሊስ አሁን የተገኘውን ሰላም ይበልጥ ለማረጋገጥ ከመቼው ጊዜ በላቀ ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑን በስነ ስርዓቱ ላይ መናገራቸውን ኢቢሲ ዘግቧል ።

The post የኦሮሚያ ክልል መንግስት የክልሉን ሠላም በማረጋገጥ ሂደት የላቀ ሚና ለተጫወቱ የፀጥታ አካላት የዕውቅና ስነ ስርዓት እያካሄደ ነው appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply