የኦሮማራ ጥምረት የህወሃትን አፓርታይድ ለማስወገድ ነው! ( ስዩም ተሾመ )

Source: http://www.mereja.com/amharic/556866

የኦሮማራ ጥምረት የህወሃትን አፓርታይድ ለማስወገድ ነው! ( ስዩም ተሾመ )

ከህወሃት ባለስልጣናት እንደ አቦይ ስብሃት የሚገርመኝ ሰው የለም፡፡ ሰውዬው ፊት-ለፊት ስለሚናገሩ ግልፅነታቸው ይመቸኛል፡፡ ነገር ግን፣ በግልፅነታቸው ውስጥ ቅጥ-ያጣው የህወሃት ግብዝነት[…]

Share this post

One thought on “የኦሮማራ ጥምረት የህወሃትን አፓርታይድ ለማስወገድ ነው! ( ስዩም ተሾመ )

 1. ሰላማዊ ሰውን በጅምላ መጨፍጨፍ ያስንቃል እንጂ አያስመስግንም፡፡ በሰዎች ዘንድ የነበረህን ክብርና ሞገስ አላሽቆ ራቁት ያስቀራል እንጂ አያሾምም፡፡ ሰውን ለመምራራት በጅምላ መጨፍጨፍ አያስፈልግም፡፡ እንደውም ጭፍጨፋ ያራርቃል ያገነጣጥላል፡፡ የነለማ ነቀርሳ ሐሳብ መገነጣጠል ከሆነ ዓላቸውን እያሳኩ ሊመስላቸው ይችላልለ፡፡ ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ ሕዝብ ታግሎ ልክ ያስገባቸዋል እንጂ የግለሰቦችን ዓላማ ለማሳካት የሚቀበላቸው አይደለም፡፡ ይልቅ አሁን ያለውን መልካም አጋጣሚ ወደ መተሳሰብና መከባበር በመለወጥ ሰላማዊ ሀገር በመፍፀር በሀገር እድገት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ በማበርከት ስማቸው በደማቅ ቀለም ሊያስፅፉ በተገባ ነበር፡፡ አልይ ግን እንደቀድሞ ታሪካቸው የሰውነት ክብር ተነፍገው እንደ እንስሳ በሲናይ በረሀ ለሽያጭ ይቀርባሉ፡፡
  የሚያሳዝነው ግን ሚስኪኑ ህዝብ ገና ሰላሙን እኩልነቱን መከባበሩን ሳያጣጥም እንዲህ ከመሰለ ጉድ መዘፈቁ ነው፡፡
  ኢህአድግን በማዳከም ሥራ ላይ ተሰማርቶ የከረመው ኦሮማራ አመለካከትና ድርጊት አሁን ድል ወይም ሞት ይጠብቀዋል፡፡ ድል ስል ሰላሙን የማደፍረስ ተግባር ይሳካለት እንደሁ እንጂ ድል አድርጎ የቋመጠለትን ስልጣን አይቀዳጅም፡፡ ኢህአድግ አይወድቅም እንጂ ወደቀ እንኳን ቢባል ኦሮማራ ስልጣን አይቀዳጅም፡፡ ለምን ቢባል የግሞች ሰባት ዓላማ ጨቋኝ መንግስት መስርቶ ሁሉንም መብቶች ረግጦ ኢቴገን መሾም ነው፡፡ ኢቴጌን የማይቀበል ሕብረተሰብ ስለተፈጠረ ተወልዶ ካደገበት አንኮቦር ጀምሮ ተግዳሮት ስለሚገጥመው መላ ኢትዮጵያ ሳያካልል አንኮቦር ላይ በሳንጃ ይሉታል፡፡ ሁለተኛው የኦሮማራ ክንፍ በግብፅ ድጎማና ፖለቲካዊ ተልእኮ እየተደጎመ በጃዎር መሐመድ እየተመራ መላ የኦሮሚያ ሙሰኛ ባለስልጣን እያሳተፈ ወያኔንን እና ወያኔን ወለደች የተባለችውን ሚስኪን የትግራይ እናትና ልጆችዋን ስም በማጥፋት አሁን እያየነው ያለውን የዘር ማጥፋት ተግባር ወደ ሁሉም ኢትዮጵያ የማስፋፋት ተግባር በማከናወን ሰው አልባ ክልሎች መፍጠርና ኢትዮጵያን ኦሮሞ ማድረግ ነው፡፡ አይሳካም እንጂ ተሳካ እንኳል ቢባል ጠባብነትና ትምክሕተኝነት በውስጡ ያነገበው የኦሮማራ ፖለቲካ ወንዝ የማይሻገርበት ምክንያት ሁለት የማይዋሃዱ ንጥረነገር በውስጡ ያነገበ ስለሆነ ነው፡፡
  የኦሮማራ
  ይህ ድርጊት የኦነግና ግንቦት 7 ሥራ መሆኑን ተገንዝበው የኢትዮጵያ ህዝቦት እና ፖለቲከኞች ከወዲሁ ሊያጤኑበት ይገባል፡፡ በጣም በርካታ ውንብድና እያየን ነው፡፡ በጣም በርካታ ዜጎች በጅምላ ተጨፍጭፈዋል፡፡ መንግስት ዓቅሙ ካለው ችግሩን ሊያበርደው /ሊፈታው ይገባል፡፡ ዓቅም ካጣ ኣሳልፎ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ይስጥ፡፡ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች መጨፍጨፍ መገደል ከትምህርት ገበታቸው መባረር/መፈናቀል እንዲሁም በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢንዳስትሪዎች መቃጠል መውደም ሀገርን ማውደም መሆኑን ሊገነዘቡት ይገባል፡፡ ልጆቻቸውን ውጭ ሀገር ስላሰፈሩ በግድ የለሽነት በማለፍ እውነታውን ደብቀው ለተባይ ኦነግና ግሞች 7 ሊሰጡን አይገባም፡፡ ኦነግና ግቦት 7 በሕግ ሽብተኛ ከተባሉ ከነዚህ አካላት አብረው የሚሠሩ አካላት ተፈትሸው በሕግ ሊጠየቁ ይገባል፡፡ ሕዝብ ዓመፀ በሚል ሰበብ ሰላማዊን ህዝብ ስም እያጠፉ ባስታጠቁት ክላላዊ ታጣቂ (ሕገወጥ ፖሊስ) የሚገድሉ/ንፁሃንን የሚጨፈጭፉ የኦሮሚያና የአማራ ክልል ወንበዴዎች ሕግ ስር ካልወደቁ መዘዙ ከባድ ነው፡፡ የመዘዙ ሰለባ የሚሆነው ሌላው ብሔር ብቻ ሳይሆን ንፁሃን የአማራና ኦሮሞ ተወላጆችም ጭምር ናቸው፡፡ ለዚህም መገለጫው በመቱ የተገደሉ የአማራ ክልል ተወላጅና ከኢ/ሶማሌ ብ/ክልል የተፈናቀሉ የኦሮሚያ ክልል ተወላጆች ምስክሮች ናቸው፡፡ ገና በእንዲህ ከቀጠለ ሶቆቃው በየክልሉ በላባቸው ለሚተዳደሩ ንፁሃን ዜጎች የሚተርፍ መዘዝ ይሆናል፡፡ ስለኢህ የመንግስት አካላት በጥንቃቄ ሊያጤኑበት ይገባል፡፡

  Reply

Post Comment