“የኦሮሞና አማራ ትብብር አማራጭ የሌለው የህልውና ጉዳይ ነው!” – ከስዩም ተሾመ

Source: http://www.zehabesha.com/amharic/?p=82547

የአምቦ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት ስዩም ተሾመ በማህበራዊ ድረ-ገጾች ሳይታክቱ ፖለቲካዊ ሀሳቦቻቸውን በማካፈል ይታወቃሉ። መምህር ስዩም ከቃሊቲ ሚዲያ ጋር በነበራቸው ቆይታ “ከሰሞኑ የኢህአዴግ አባል ድርጅት በሆነው የኦሮሞ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኦ.ህ.ዴ.ድ) የሚታየው አዳዲስ ሁኔታዎች የምን መገለጫዎች ናቸው? ወቅታዊ የፖለቲካ ፕሮፖጋንዳ ወይስ ውስጣዊ የአስተሳሰብ ለውጥ?” በሚል አርስት ዙሪያ ተወያይተዋል። ከዚህ በተጨማሪ፣ ይህን “የአንድ_ነን፣ አንለያይም…” የሚሉ ስሜቶች ባለቤት ማን ነው? ህዝቡ ወይስ ፓርቲው? የሀገሪቱ ህዝብ ሁለት ሶስተኛውን የያዙት አማራና ኦሮሞ አንድ ነን ሲሉ በሌላ በኩል የሚሰማው ድምጽ የምን ድምጽ ነው? ለምን? በኦ.ህ.ዴ.ድ ውስጥ የታየው የህዝባዊ አንድነት መንፈስ ወደ ሌሎቹ የኢህአዴግ ፓርቲዎች ይጋባል ወይስ …? ነገሮች ወዴት እያመሩ ነው? በእነዚህና ሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ያደረግነውን ቃለ ምልልስ ይህን ማያያዣ (link) በመጫን እንድታዳምጡ ተጋብዛችኋል፡፡

Share this post

One thought on ““የኦሮሞና አማራ ትብብር አማራጭ የሌለው የህልውና ጉዳይ ነው!” – ከስዩም ተሾመ

 1. ..መምህር ስዩም ተሾመ “ከሰሞኑ የኢህአዴግ አባል ድርጅት በሆነው የኦሮሞ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኦ.ህ.ዴ.ድ) የሚታየው አዳዲስ ሁኔታዎች የምን መገለጫዎች ናቸው?
  ++ ይህ ነገር ሌንጮ ባቲን ያስታውሰኛል…ብሔራዊ ንቅናቄ(የብሔር አላልኩም!) ማኅበር ለመመሥረት ከሚታወቁና ከታጠቁ አርበኞች፡ ልሂቃንና የመስከረም ፪ ታጋዮችን ጨምድደው በሀገረ አሜሪካ ሲዋቀሩ አማራ በአንድ የማስፈራሪያ ታዛቢ ተወካይ ጥግ ቆሞ ነበር። አንድ ጠያቂ “ይህ ሁሉ አንድነት ከልባችሁና ነው? በሉዓላዊት ኢትዮጵያ(አንገነጠልም) ብላችሁ ለመኖር ወስናችሁ ነው? አብዛኛው የዲያስፐር ተቃዋሚ ዛሬ ለምን እዚህ አልተገኙም?” ሲል አፍረጠረጠው ”
  ዶ/ር ሌንጮ ባቲም ይላሉ
  “እርግጥ ነው ድሮ እኛ ፖለቲካውን ያስተማርናቸው ዛሬ ከጎናችን የሉም!…ወጣቱ(ቂሮ) ገና ምን እንደሚፈልግ ውሳኔው ገና አልታወቀም፤አለየለትም! እርግጠኛ ባልሆንበት መዋሸትና ተስፋ መስጠት አንፈለግም!”። አሉ ሌሎችም ይህንን እየሸራረፉም ይሁን እየጠገኑ “ከኦሮሞ ተዋልደናል ተጋብተናል ትላላችሁ ከኦሮሞ የተዋለደና የተጋባው ቁጥር እጅግ በጣም ጥቂት ነው እኛን ከትግል አይከለክለንም አያግደንም!ሲሉም ምሁራዊ ትንታኔ ሰጡ። ይህን ሲሉ ከሁለት ነገድ የተወለዱትን መጤና ሰፋሪ አድርገው በሁለተኛ ዜግነት አንቋሸው ከህወሓት ማኒፌስቶ እንደምን ተለዩ? ዶ/ር በያን አሶባ ደግሞ አዲሲቷ ኢትዮጵያ እያለ ሲደነፋ ቆይቶ…”ባለችው ኢትዮጵያ ፍትሕና እኩልነት ማለት ምንድነው? የምን ኢትዮጵያ? የቷ ኢትዮጵያ? ሲልም ብሔራዊ ንቅናቄው የህወሓትን’የዲሞክራሲያዊ ብሔርተኝነት’አድናቂና አስራጭ(ጺ) ይሆናል፡፡ በኋላማ የኦሮሞ ወጣት አራት ሰንደቅ ይዞ ደርትና ግንባሩ ለጥይት ዒላማ ሲሆን እያየ አረንጓዴ፤ ቢጫ፤ ቀይ፤ ሰንደቅን በውይይት አልወሰንም የሚለው ሌንጮ ለታ…፳ሺህ የኦእነግ ሚሊሻ ለህወሓት ገብሮ፡ ማኒፌስቶውን በሕገመንግስት ጭብል ሸጦ፡ ከሀገር በክብር ሲሸኝ …የሚኩራራበት ነገር ቢኖር “ሃሌ ሉያ ያልጠበቅነውን መሬት ማግኘታችን” ይለዋል። የኦሮሞ ወጣት ግን ዛሬም ይህንን ሁሉ ካርታ ይዞ የበይ ተመልካች፤ የስታዲየምና የኮንደሚኒየም ልዩ ተመጽዋች፡ መሆኑ ቂጡን በግሩ እየመታ እንዲጨፍር በክልል ታጉሮ በኢትዮጵያዊነቱ እንዲያፍር የተደረገው በሥልጣን ርሃብተኛው ዲያስፐር የቡልጠቃ ባዶ ወሬ ቱማታ ድንፋታ ነው።
  ወቅታዊ የፖለቲካ ፕሮፖጋንዳ ወይስ ውስጣዊ የአስተሳሰብ ለውጥ?”
  ++ ከላይ ከታሪክ የምንረዳው ህወሓት የድሮ ታጋይ ኦነጎችን ለቤተሰብ ለቀሶ ለመድረስ፡ ይሁን የሠላማዊ ፓርቲ ለመመሥረት ልዩ ፍቃድ ሰጪም ነሺም ነውና…እየተረገጥን እየተተፋብን ኖረናል ካሉት ጁነዲን ሳዶ የኢሳት ላይ ቱሪናፋ፡ በተቃራኒው ለፖለቲካው ሞቅታ…የሁለት ክልላዊ ቤተሰቦች ታይቶ እንደማይተዋወቅ የውጭ ዜጋ ያደረጉት የተጋነነ ነገር ቢበዛውም የጎጃምን ጤፍ ማሳ በዓይን ማየታቸው ብቻ ጎጃም ድረስ ሀገር እንዳላቸው ማወቃቸውም ችግሩ አለመቀራረብ እንጂ መራራቅ እንደሌለ የጤፍ ማሳን ከመኪና ላይ መለየታቸው…ኢትዮጵያዊ ማንነት የለም! ለሚለው ኦሮሞው ጸጋዬ አርአንሳ እንጀራና ወጥ የትግሬና የአማራ ብቻ ሳይሆን የኦሮሞም መገለጫ መሆኑን ተምሮበታል…፪፻፶ ኦሮሞ ሲጓዝ፡ የራሱን ምግብና ልብስ ይዞ ተጓዘ?ወይስ ያንኑ ብልኮ ነጭ ልብስ ልብሶ አረቄ (የግብጦ)እና የገብስ ጠላ ከሽክሾ “ኢትዮጵያ ኬኛ ሲል አደረ!?

  ይህን “የአንድ_ነን፣ አንለያይም…” የሚሉ ስሜቶች ባለቤት ማን ነው? ህዝቡ ወይስ ፓርቲው?
  ++ ኦህዴድና ባዴን አንለያይም ካሉ ነገር አለ…ብሔር ብሔረስቦች ባጣ ቆይኝ ካርድ ሆነዋል፡ታዳጊ ክልል እየተባሉ በአማራ ሥም እረጅም ጦር ተሰብቆባቸው በሚያሳፍርና በሚያሳዝን ቅላፄ ተረስተዋል።ህወሓት አማራን ጥሎ የአብዲ ኢሌን ሚሊያሻ ይዞ ሻቢያ ሥር ተሸጉጦ ከአጋም የተጠጋ ቁልቋል አድርጎ ትግሬን ዳግም ሰው እንዳይሆን ወገን አልባ ያደርገዋል ማለት ነው።
  **የሕዝብ አንለያይም ከሆነ ግን ሰው በሰውነቱ እንዲከበር፡ ጥላቻ ተወግዶ፡ አብሮ ሠርቶ አብሮ ለማደግ፡ ሸረኛ! ምቀኛ!አድርባይ! አቀጫጭ የዘረኝነትና ጎጠኝነት አረምን መንቀል ማለት ነው። ከአንድነትና አብሮነት የበለጠ ጸጋ የለም!!

  የሀገሪቱ ህዝብ ሁለት ሶስተኛውን የያዙት አማራና ኦሮሞ አንድ ነን ሲሉ በሌላ በኩል የሚሰማው ድምጽ የምን ድምጽ ነው?
  ለምን?
  ++ “ልዩ ጥቅማጥቅመኛ” ኮንተሮባንድ፡ አየር በአየር፡ መሞሳመስ፡ እከክልኝ ልከከልህ፡ዕውቅና፡በፈጠራ ወሬና ትርክት መጽሕፍ መሸቀልና ማናቆር፡ በራሱ ልማታዊ ተጠቃሚነት ነው። ከእያንዳንዱ የገንዘብ ምንጭ ጀርባ(ኪራይ ሰብሳቢ)ደላላ፡ አቀባባይ፡ተቀባይ፡አስፈጻሚና ባለድርሻ ብሔርተኛ ቡድን አለ። ይህም በክልል ተሸጉጦ ሕዝቤ፡ቋንቋዬ፡ባህሌ፡ ታሪኬ እያለ እየዞረ ያማስላል..ግን በልቶ እያባላ ያለቅሳል።ይህ ባይሆን እንዴት ሰባት ሰው ጫካ ደርሶ ተመልሶ ፹፬ ሚሊየን ሕዝብ አጀዘበ!?
  ራዕዩ ይቀጥላል!ድሮ ሰው አልነበርንም!ማንነታችን ተረስቶ!በፌደራሊዝሙ ህገመንግስታችን ከሚነካ በአንገታችን ሜንጫ እያሉ ጭፍን/ዕውር ተቃዋሚ ስለሆኑ ብቻ ነው። “ሰዶ ማሳደድ ሲያምርህ ኢትዮጵያን በክልል ቀይር”.>>>

  በኦ.ህ.ዴ.ድ ውስጥ የታየው የህዝባዊ አንድነት መንፈስ ወደ ሌሎቹ የኢህአዴግ ፓርቲዎች ይጋባል ወይስ …?
  ነገሮች ወዴት እያመሩ ነው?
  ++ አሁን ሁሉም የአንድነት መረብ እየሰራ ነው፡ ማጥመጃ ነው መጥለፊያ ነው!? ሀገራዊ ፋይዳ አለው? ወይስ ክልላዊ ብሔርተኝነት..ሥርዓተ አልበኝነት፡ ዘረኝነት፡ተክሎ በጩቤና ሜንጫን ሲቀነጥሱ መኖር!?አቃሚውም ተጠቃሚው ህወሓት ነው!። ልብ ያለው ትውልድ ቢኖረን የእንዲህ ነበርን ቁርሾ ትቶ፡ በወደፊቱ ላይ ከደርግም ከህወሓትም ለየት ያለ ሰው ሆኖ ፍርሃ እግዝሐብሔር ያደረበት፡ ተናግሮ የሚደመጥ፡ሠርቶ የሚያሰራ ከማናቸውም ነገድ ቢገኝ ቀናው የለውጥ መንገድም ያ ነው። **ትውልድ እንደከብት በክልል አጉሮ እንደፈለጉ እየነዱ ማምከንና ማባከን ግን ይቅርታ የማያሰጥ ኢ-ሰብዓዊነት ነው።
  ሰው(ዬው)(ይቱ) (ዎቹ) ማነው እነማን ናቸው።ሆድ ከሀገር ይሰፋልን!?።

  Reply

Post Comment