የኦነግና የኦዴፓ ውዝግብ አገራዊ አንድምታ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/79499


ብሩክ አብዱ Reporter Amharic

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ወደ ሥልጣን ከመጡበት መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም. ወዲህ በተለያዩ ምክንያቶች ከኢትዮጵያ ርቀው በውጭ ሲንቀሳቀሱ የቆዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ወደ አገር ቤት እንዲመለሱና ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል እንዲያደርጉ በተደጋጋሚ ጥሪዎች ሲያደርጉ ተደምጠዋል፡፡ ይኼንን ጥሪ በመከተልም ካሁን ቀደም በጉልህ ስማቸው የሚታወቁም ሆነ የማይታወቁ የፖለቲካ ቡድኖች ወደ አገር ቤት ተመልሰው ለመታገል የሚያስችላቸው ሁኔታ በመፈጠሩ እንደተመለሱ እየተናገሩ፣ ገሚሱ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የተቀሩት ደግሞ በተለያዩ መጓጓዣዎች ድንበር አቋርጠው ገብተዋል፡፡
እነዚህ የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ አገር ቤት ከገቡ አንስቶ በስፋት የፖለቲካ ሥራዎችን ሲያከናውኑ ባይታዩም፣ አንዳንዶቹ የውይይት መድረኮችን በማዘጋጀት ሕዝብን ማወያየት፣ በተለያዩ የፖለቲካ ውይይቶች ላይ እሳቤዎቻቸውንና አቋሞቻቸውን ማንፀባረቅና በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በመዘዋወር ደጋፊዎቻቸውን ሲያነቃቁ ተስተውለዋል፡፡ በዛ የሚሉት በአገሪቱ የተጀመረውን ለውጥ ለማስቀጠል ያግዛሉ ባሏቸው ዘርፎች ከመንግሥት ጋር በመተባበር ለመሥራት ፍላጎት ሲያሳዩ፣ የተወሰኑት ራቅ ብለው በመጓዝ የገዥው አዲስ አባል ድርጅት ከሆኑ ፓርቲዎች ጋር አብሮ ለመሥራት የሚያስችላቸውን ስምምነት እስከ መፍጠር ደርሰዋል፡፡ ከእነዚህም መካከል ከኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዴፓ) ጋር ተዋህኦ ለመቀጠል የመግባቢያ ሰነድ የተፈራረመው በአቶ ሌንጮ ለታ የሚመራው የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኦዴግ) እና ውህደት የፈጸሙት የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) እና የአማራ ዴሞክራሲ ኃይል ንቅናቄ (አዴኃን) ይጠቀሳሉ፡፡
የኦነግና የኦዴፓ ውዝግብ አገራዊ አንድምታ
ይሁንና በመንግሥት ጥሪና በተለየ ድርድር ወደ አገር ቤት የተመለሰው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) በተመለከተ የሚታየው ግን የመተባበርና አብሮ የመሥራት ሳይሆን ተገዳዳሪነት የሚታይበት ነው ሲሉ፣ በርካታ ፖለቲከኞችና

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.