የኦነግ መግለጫ: የኢሕኣዴግ ሠራዊት በሰላማዊ ዜጎች ላይ እየፈጸመ ያለውን ግድያ በጥብቅ እናወግዛለን !

Source: https://mereja.com/amharic/v2/79555

ታህሳስ 27, 28 እና 29, 2018 ዓም በምዕራብና ደቡብ ኦሮሚያ (ቄሌም ወለጋ, ምዕራብ ወለጋና ጉጂ) ዞኖች ውስጥ ብቻ “የሃገር መከላከያ ሠራዊት” በሚል የሚታወቁ የኢሕኣዴግ ወታደሮች በሰላማዊ (ትጥቅ-ኣልባ) የኦሮሞ ዜጎች ላይ በፈጸሙት ዘግናኝ ግድያ እስካሁን በተረጋገጠ መረጃ ቢያንስ 36 የሚሆኑ ሰዎች ተገድለው ቁጥራቸው እስከ ኣሁን በውል ያልታወቀ ደግሞ ቆስለዋል።

በርካታ የህዝቡ መኖሪያ ቤቶችም በእሳት ጋይተዋል። የኢህኣዴግ ጦር ሃይል ኣባላት እየወሰዱት ባለው በዚህ በእጅጉ ኣስከፊና አረመኔያዊ እርምጃ ከተገደሉት ዜጎች መካከል ሁለት እድሜያቸው 5 ዓመት ያልሞላቸው ህጻናት በጉጂ ዞን ዱግዳ ዳዋ ወረዳ ከቤት ጋር እንዲቃጠሉ ተደርገዋል። በምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢና ጉሊሶ መካከል በሚገኝ ኩርፌ ብርብር በተባለ ቦታም ኣንድ ህጻን ከወላጅ እናት ጋር ከነቤታቸው ተቃጠሉ። እነዚህን መሰል የግድያ ወንጀሎች የተፈጸሙባቸው ቦታዎች በቄሌም ወለጋ፡ ምዕራብ ወለጋና ጉጂ ዞኖች ውስጥ ጊዳሚ፡ ኮበረ፡ ከታ ኣባ-ኮርማ፡ ሁዋ፡ ዋዪ ኩሊ፡ ኩርፌ ብርብር፡ ዩብዶ፡ ላሎ ቂሌ፡ ፊንጫኣ፡ ኮምቦልቻና ሻላ በተባሉ ቦታዎች ውስጥ ነው። በጉጂ ከተገደሉት 23 ከሚሆኑት መካከል 5 ዓመት ያልሞላቸው ህጻናትና የ70 ዓመት ኣዛውንት ይገኙበታል።

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር በሰላማዊ (ትጥቅ-ኣልባ) ሰዎች ላይ በኢህኣዴግ ወታደሮች እየተፈጸመ ያለውን ኣሰቃቂ፡ ግድያ ኣጥብቆ ያወግዛል። ይህን መሰሉ የኣውሬነት ኣረመኔያዊ እርምጃም በዝምታ መታየት የሌለበትና በሁሉም ሰላም-ወዳዶች መወገዝ ያለበት ነው ብለንም እናምናለን። የጭቆናና ኣምባገነናዊ ስርዓት (በጠብመንጃ ኣፈሙዝ ህዝብን የሚገዛ) ካሁን በኋላ እንደማይቻል ለኢህኣዴግ ፓርቲ ለማሳየት ለመገመት የሚያዳግት የህይወትና የንብረት መስዋእትነት ተከፍሎበታል። የኢህኣዴግ ፓርቲም ከ27 ዓመታት በኋላ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.