የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ነጥብ ይፋ ሆነ

Source: https://fanabc.com/2019/09/%E1%8B%A8%E1%8A%A8%E1%8D%8D%E1%89%B0%E1%8A%9B-%E1%89%B5%E1%88%9D%E1%88%85%E1%88%AD%E1%89%B5-%E1%88%98%E1%8C%8D%E1%89%A2%E1%8B%AB-%E1%8A%90%E1%8C%A5%E1%89%A5-%E1%8B%AD%E1%8D%8B-%E1%88%86%E1%8A%90/

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 6፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የ2012 የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ነጥብን በዛሬው እለት ይፋ አድርጓል።

በዚሁ መሰረት፦

በተፈጥሮ ሳይንስ

ለወንድ 176

ለሴት 166

በማህበራዊ ሳይንስ

ለወንድ 174

ለሴት 164

ለታዳጊ ክልሎች

በተፈጥሮ ሳይንስ

ለወንድ 166

ለሴት 156

በማህበራዊ ሳይንስ

ለወንድ 164

ለሴት 154

ልዩ መቁረጫ ነጥብ

መስማት ለተሳናቸው በተፈጥሮ እና በማህበራዊ ሳይንስ

ለወንድ 120

ለሴት 115

አይነ ስውራን በማህበራዊ ሳይንስ ብቻ

ለወንድ 110

ለሴት 105

ለግል ተፈታኞች በማህበራዊ እና በተፈጥሮ ሳይንስ

ለወንድ 190

ለሴት 185

አጠቃላይ ወደ ግል የትምህርት ተቋማት ገብተው ለመማር ለሚፈልጉ የማለፊያ መቁረጫ ነጥብ ደግሞ 140 መሆኑን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ቅበላ የሚያገኙ ተማሪዎች በተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ 46 ሺህ 416፣ ሴት 32 ሺህ 865 በድምሩ 79 ሺህ 281 ሲሆኑ ፥ በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ ወንድ 34 ሺህ 838 ሴት 28 ሺህ 702 በድምሩ 63 ሺህ 540 መሆናቸው ተገልጿል።

በዚህ መሰረትም ወደ መንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ከሚገቡ ተማሪዎች 55 ነጥብ 5 በመቶ የሚሆኑት የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ሲሆኑ፥ 44 ነጥብ 5 በመቶዎቹ ደግሞ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ናቸው።

ሚኒስቴሩ በመግለጫው ላይ እንዳስታወቀው፥ በዘንድሮው ዓመት በአጠቃላይ ወደ መንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚገቡ ተማሪዎች ቁጥር 142 ሺህ 821 ነው።

የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች መግቢያ አራት መሰረታዊ የትምህርት አይነቶችን ውጤት መሠረት አድርጎ እንደሚወሰን መገለጹ ይታወሳል።

የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ነጥቡ የሚቆረጠው በእንግሊዝኛ፣ በሂሳብ፣ የስኮላስቲክስ አፕቲቲዩድ፣ ከተፈጥሮ ሳይንስ በፊዚክስ፣ ከማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ በጂኦግራፊ የትምህርት ዓይነቶች ነው።

የዘንድሮውን የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ በአራት የትምህርት ዓይነቶች ብቻ እንዲወሰን የተደረገው የጋሸበና የተጋነነ የፈተና ውጤት በመታየቱ መሆኑን የትምህርት ሚስቴርና የክልል የትምህርት ቢሮዎች በጋራ በሰጡት መግለጫ መግለጻቸው አይዘነጋም።

በ2011 ዓ.ም የዩኒቨርስቲ መግቢያ (የ12ኛ ክፍል) ፈተና ለመውሰድ ከተመዘገቡት 322 ሺህ 717 ተማሪዎች መካከል 319 ሺህ 264 የሚሆኑት ፈተናውን ወስደዋል።

 

በሀይለእየሱስ ስዩም እና በዙፋን ካሳሁን

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.