የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው።

Source: https://mereja.com/amharic/v2/204510

የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ በኢትዮጵያ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ታውቋል፡፡
የካናዳ መንግስት ልዑክም ዛሬ ከኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጋር ተወያይቷል፡፡ በውይይታቸው የካናዳ መንግስት ከኢትዮጵያ ጋር በንግድ፣ ፀጥታን በማስከበር እንዲሁም በሥርዓተ ፆታ ዘርፎች አብሮ ለመስራት ፍላጎት እንዳለው ልዑኩ ለፕሬዝዳንቷ አስረድቷል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ በኢትዮጵያ ስላቀዱት ጉብኝት እንደተወያዩም ታውቋል፡፡

ኢትዮጵያ እና ካናዳ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን የመሠረቱት በአውሮፓውያኑ 1965 ነው፡፡ በምሥራቅ አፍሪካ ኢትዮጵያ ሠላምን በማስተዋወቅ እያካሄደች ላለችው አስተዋፅዖ ካናዳ እውቅና ትሰጣለች፡፡ ሀገሪቱ የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት፣ ሙስናን ለመዋጋት፣ሴቶችን በልማትና በፖለቲካ ለማሳተፍ የምታደርገው ጥረትም በካናዳ መንግስት የሚበረታታ ነው፡፡
ኢትዮጵያ እና ካናዳ ዓመታዊ የሁለትዮሽ ስልታዊ ምክክርም አላቸው፡፡ በንግድና መዋዕለ ንዋይ ፍሰት፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ በአካባቢና አየር ንብረት ለውጥ፣ በትምህርትና ባህል ላይም ይተባበራሉ፡፡
በአውሮፓውያኑ ከ2017 እስከ 2018 ባሉት ጊዜያት ኢትዮጵያ ከካናዳ 198 ነጥብ 15 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ ተደርጎላታል፡፡ ካናዳ ለኢትዮጵያ የምታደርገው እርዳታም የምግብ ዋስትና እና ምርታማነትን በማሳደግ፣ የዴሞክራሲ አስተዳደር ስርአትን በመገንባት፣ የሰብዓዊ መብቶችን በማጠናከር እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ በማተኮር የሚከናወን ነው፡፡
በንግዱ ዘርፍም በአውሮፓውያኑ 2018 ያካሄዱት የሁለትዮሽ የንግድ ልውውጡ በጠቅላላው ከ170 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ደርሷል፡፡ ካናዳ የምትልካቸው ምርቶች በገንዘብ ሲተመኑም 130 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ ያወጣሉ፡፡ በአንፃሩ ካናዳ ከኢትዮጵያ የምታስገባቸው ምርቶች 40 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ ናቸው፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝትም ጀምር ትብብሮችን ለማጠናከርና የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት ዕድሎች በቅርበት ለመመልከት ዕድል ይፈጥርላቸዋል፡፡ የጉብኝቱ ቀን ባይቆረጥም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ኢትዮጵያ ይዘዋቸው የሚመጡት

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.