የኮሮና ወረርሽኝ – የምርጫ ዘምቻ የጀርመን ልምድ እና አስተያየት በሕገ-መንግስት ላይ-ክፍል 6 – ፀጋዬ ደግነህ (ዶ/ር)

Source: https://www.zehabesha.com/amharic/archives/106969

ለተከበራቹህ ወገኖች የኮሮና ወረርሽኝ እና ምርጫ በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት የኢትዮጵያ ምርጫ መራዘሙን በተመለከተ ስለጀርመን ምርጫ ልምድ ለመግለፅ በአጭሩ እሞክራልሁ። የኢትዮጵያ ምርጫ ለመራዘሙ ምክንያት ተደርጎ የሚሰማው በወረርሽኙ የተነሳ የበለጠ ሊያጋልጥ የሚችለው ወይም አስቸጋሪው የምረጡኝ ቅሰቀሳ ዘመቻ፣ የምርጫው ሂደት እና በምርጫው ቀን ለማስፈፀም እንደማይቻል ነው። የጀርመንን ልምድ ከወሰድን ምርጫ በየ4 ዓመቱ ሲደረግ ይህም ከፍተኛ በሆነ፣ ለወራት በሚቆይ በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብን ባሳተፍ የምርጫ ዘምቻ የሚካሄድ ነው። የምርጫ ዘመቻ የፖለቲካ ግንኙነትን ከህዝብ ጋር ማጠናከሪያ እና ማሳተፊያ ተድርጎ ይወሰዳል። ከምርጫው በፊት በስልጣን ላይ ያለ ፓርቲም ሆነ ተፎካካሪ ወገኖች ሁኔታውን ለመመርመር እና የወደፊቱ እቅዶቻቸውን  የሚያስተዋውቁበት እድል የሚፈጠርበት ነው፡፡ ተምራጮችም የመመርጥ ድምፅን  ለማብዛት (Vote-maximizing) ለማድረግ እና ካለፈው ምርጫ በኋላም የተዳከመውን የፓርቲ እና ህዝብ ግንኙነቶች ለማደስ የሚሄዱበት መንገድም ነው። ይህም ለከፍተኛ አገርን ለመምራት የሚሰየሙትን የፖለቲካ እጩ ተወዳዳሪዎቻቸው ላይ የህዝቡን እምነት

The post የኮሮና ወረርሽኝ – የምርጫ ዘምቻ የጀርመን ልምድ እና አስተያየት በሕገ-መንግስት ላይ-ክፍል 6 – ፀጋዬ ደግነህ (ዶ/ር) appeared first on ዘ-ሐበሻ: ZeHabesha Latest Ethiopian News Provider.

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.