የኮይሻ ኃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በፋይናንስ እጥረት ምክንያት ተስተጓጎለ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/79507

የበጀት ዓመቱን የስድስት ወራት ሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለማቅረብ ዓርብ ታኅሳስ 19 ቀን 2011 ዓ.ም. በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተገኙት የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) የኮይሻ ኃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በፋይናንስ እጥረት ምክንያት መስተጓጎሉን አመኑ፡፡
ሚኒስትሩ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተፈጥሮ ሀብት፣ መስኖና ኢነርጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እንዳሉት የኮይሻ ፕሮጀክት ከፍተኛ የፋይናንስ ችግር ገጥሞታል፡፡ በዚህ ዓመት ምን ደረጃ ላይ ይደርሳል የሚለውን ጉዳይ አሁን ላይ መናገር አይቻልም ብለዋል፡፡
የቋሚ ኮሚቴው አባላት በሚኒስትሩ የቀረበውን ሪፖርት በመገዳደር ፋይናንስ ሳይገኝ እንዴት ፕሮጀክት ይጀመራል? የጀመራችሁትን ፕሮጀክት ምን ደረጃ ላይ እንደሚደርስ እንዴት አታውቁም? በማለት ጥያቄዎች አቅርበዋል፡፡
ሚኒስትሩ ለጥያቄዎቹ በሰጡት ምላሽ፣ መንግሥት ኮንትራክተሩ ላከናወነው ሥራ መከፈል የነበረበትን 250 ሚሊዮን ዮሮ መክፈል አልቻለም፡፡ የፕሮጀክቱን የፋይናንስ ችግር ለመፍታት ከሚኒስትሮች የተውጣጣ ኮሚቴ ተቋቁሟል ብለዋል፡፡
‹‹ይህንን የኮይሻ ፕሮጀክት በመንግሥትና በግል አጋርነት እንዲካሄድ እየታሰበ ነው፤›› በማለት፣ ይህ ፕሮጀክት የገጠመውን የፋይናንስ ችግር ሚኒስትሩ አብራርተዋል፡፡
የኮይሻ  ኃይድሮ ኤሌክትሪክ ማመንጫ ፕሮጀክት ሙሉ ለሙሉ እንዲካሄድ የታሰበው በአጭር ጊዜ የሚከፈልና ከፍተኛ ወለድ በሚከፈልበት ኮሜርሻል ብድር ነው፡፡
ብድሩ የተገኘው ግንባታውን ለማካሄድ ውል ገብቶ በተረከበው ሳሊኒ ኮንስትራክሽን ኩባንያ አማካይነት ሲሆን፣ ሥራው ውስጥ ከተገባ በኋላ በተለያዩ ምክንያቶች ብድሩ መለቀቅ አልቻለም፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አብርሃም በላይ (ዶ/ር) ኅዳር 25 ቀን 2011 ዓ.ም. ይህ ፕሮጀክት በፋይናንስ ችግር ምክንያት መስተጓጎሉን ለገንዘብ ሚኒስቴር ገልጸው ነበር፡፡
እሳቸው በወቅቱ እንደገለጹት የኢትዮጵያ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.