የወረዳ የትሥሥር መረብ አቅምን ለማሻሻል እየተሰራ ነው ተባለ

Source: https://fanabc.com/2019/11/%E1%8B%A8%E1%8B%88%E1%88%A8%E1%8B%B3-%E1%8B%A8%E1%89%B5%E1%88%A5%E1%88%A5%E1%88%AD-%E1%88%98%E1%88%A8%E1%89%A5-%E1%8A%A0%E1%89%85%E1%88%9D%E1%8A%95-%E1%88%88%E1%88%9B%E1%88%BB%E1%88%BB%E1%88%8D/

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የወረዳ የትስስር መረብ አቅምን ለማሻሻል እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር አህመዲን መሃመድ እንዳሉት ሃገሪቱን በቴክኖሎጂው መስክ የማሸጋገር እንዲሁም በቀላሉ ስራን ማሳለጥ ላይ እየተሰራ ያለውን የማሻሻያ እንቅስቃሴ በማሳካት ረገድ ሚኒስቴሩና ኢትዮ ቴሌኮም ሁለቱ ተቋማት ያላቸው ሚና ተመጋጋቢ በመሆኑ በዘርፉ ውጤታማ ለመሆን በጋራ የሚሰሩ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ።

አያይዘውም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የኢትዮ ቴሌኮም በወረዳ የትሥሥር መረብ የሚሰጠውን አገልግሎት የበለጠ ለማቀላጠፍ የሚያስችሉ ስራዎችን እየሰሩ ነው ብለዋል።

በሌላ በኩል የወረዳ የትሥሥር መረብ አገልግሎት የሚያገኙ ተቋማትን ፍላጎት ባማከለ መልኩ የመረጃ ፍሰት መጠኑን ወደ በሰከንድ 10 ጊጋ ባይ ለማሳደግ ይሰራል መባሉን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.