የዋሽንግተን ዲሲ ከንቲባ ሙሪየል ቦውሰር አዲስ አበባ ገቡ

Source: https://fanabc.com/2019/11/%E1%8B%A8%E1%8B%8B%E1%88%BD%E1%8A%95%E1%8C%8D%E1%89%B0%E1%8A%95-%E1%8B%B2%E1%88%B2-%E1%8A%A8%E1%8A%95%E1%89%B2%E1%89%A3-%E1%88%99%E1%88%AA%E1%8B%A8%E1%88%8D-%E1%89%A6%E1%8B%8D%E1%88%B0%E1%88%AD-2/

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካዋ ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ከንቲባ ሙሪየል ቦውሰር ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል።

ከንቲባ ሙሪየል ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲድርሱም ምክትል ከንቲባ ኢነጂነር ታከለ ኡማና የተለያዩ የከተማዋና የፌዴራል ክፍተኛ የስራ ሃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ከከንቲባዋ ጋር ከ50 በላይ በተለያዩ የስራ ዘርፎች ላይ የተሰማሩ የንግድ ማህበረሰብ አባላት አዲስ አበባ መግባታቸውን ከከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከንቲባዋ ወደ አዲስ አበባ የመጡትም ከዚህ ቀደም ምክትል ከንቲባ ኢንጂነርር ታከለ ኡማ በዋሽንግተን ዲሲ ባደረጉት ጉብኝት ወቅት ባቀረቡላቸው ግብዣ መሰረት ነው።

ከንቲባዋ በመዲናዋ በሚኖራቸው ቆይታም የተለያዩ ጉብኝቶችን የሚያደርጉ ሲሆን፥ አዲስ አበባና ዋሽንግተን ዲሲም የእህትማማች ከተማነት ስምምነታቸውን የሚያጠናክር ስምምነት የሚፈራረሙ ይሆናል።

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.