የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማቶች ጋር የትውውቅ ፕሮግራም እያደረጉ ነው  

Source: https://fanabc.com/2019/05/%E1%8B%A8%E1%8B%8D%E1%8C%AD-%E1%8C%89%E1%8B%B3%E1%8B%AD-%E1%88%9A%E1%8A%92%E1%88%B5%E1%89%B5%E1%88%A9-%E1%8A%A8%E1%89%B0%E1%88%88%E1%8B%AB%E1%8B%A9-%E1%88%80%E1%8C%88%E1%88%AB%E1%89%B5-%E1%8B%B2/

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 14 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ካደረጉ የውጭ ሀገር ዲፕሎማቶች ጋር የትውውቅ ፕሮግራም እያደረጉ ነው።

በስካይ ላይት ሆቴል እየተካሄደ ባለው የትውውቅ ፕሮግራም ላይ የተለያዩ ሃገራት ዲፕሎማቶች ተገኝተዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከዲፕሎማቶቹ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ባለፈው ሚያዚያ 10 ቀን 2011 ዓ.ም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው መሾማቸው የሚታወስ ነው።

 

 

በስላባት ማናዬ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.