የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱን ጨምሮ ኢትዮጵያን በተለያዩ ሀገራት የሚወክሉ አምባሳደሮች የሸገርን ማስዋብና የእንጦጦ ፓርክን ጎበኙ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱን ጨምሮ ኢትዮጵያን በተለያዩ ሀገራት የሚወክሉ አምባሳደሮች የሸገርን ማስዋብና የእንጦጦ ፓርክን ጎበኙ

አዲስ አበባ ፣ጳጉሜን 3 ፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያን በተለያዩ ሀገራት የሚወክሉ አምባሳደሮች የሸገርን ማስዋብና የእነጦጦ ፓርክን ጎብኝተዋል ።

በጉብኝቱ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸውን ጨምሮ በአመታዊው የአምባሳደሮች ስብሰባ ላይ የተካፈሉ አምባሳደሮችና የቆንሥላ ፅህፈት ቤት ኃላፊዎች ተሳትፈዋል ።

በጉብኝቱ ላይ የተሳተፉት አምባሳደሮችም ÷ ፕሮጀክቶቹ ልዩ ስሜትን እንደፈጠሩባቸው ገልፀው÷ ሀገርን በሚገባው ልክ ለማስተዋወቅ የሚጠቅሙ የትውልድ አሻራዎች ማሳያ ናቸው ብለዋል።

ፕሮጀክቶቹ በብዙ መንገድ ገጽታን ከመቀየራቸውም በላይ የመቻል አብነት የሚሆኑ ናቸውም ነው ያሉት።

ከዚያም ባለፈ ሀገርን ለማስተዋወቅ ለሚደረገው ወሳኝ ስራም ግዙፍ ሚና ይኖራቸዋልም ብለዋል።

በሀብታሙ ተ/ስላሴ

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

The post የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱን ጨምሮ ኢትዮጵያን በተለያዩ ሀገራት የሚወክሉ አምባሳደሮች የሸገርን ማስዋብና የእንጦጦ ፓርክን ጎበኙ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply