የዓለም ቱሪዝም ቀን በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው

Source: https://fanabc.com/2019/10/%E1%8B%A8%E1%8B%93%E1%88%88%E1%88%9D-%E1%89%B1%E1%88%AA%E1%8B%9D%E1%88%9D-%E1%89%80%E1%8A%95-%E1%89%A0%E1%8A%A0%E1%8B%B2%E1%88%B5-%E1%8A%A0%E1%89%A0%E1%89%A3-%E1%8A%A8%E1%89%B0%E1%88%9B-%E1%8B%B0/

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የዓለም ቱሪዝም ቀን በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው፡፡

የዓለም ቱሪዝም ቀንን አስመልክቶ በዛሬው እለት ከስድስት ኪሎ እስከ እንጦጦ ማርያም ተራራ ድረስ የእግር ጉዞ ተደርጓል፡፡

በእግር ጉዞው ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ ኪነ ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባየን ን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት አምሳደሮች እና ዲፕሎማቶች ታድመዋል፡፡

የቱሪዝም ባለሙያዎችና የተለያዩ ሆቴል ተወካዮችም በእግር ጉዞው ፕሮግራም መሳታፋቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽህፍት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.