የዕውቀት ፀሀይ ሳትወጣ የጠለቀችበት አባይ ፀሀዬ (በድንበሩ ደግነቱ)

Source: http://amharic.abbaymedia.info/archives/42699

የአሜሪካ መስራች አባቶች ከሁለት ክፍለ ዘመናት ቀደም ብለው የሕዝብ ቆጠራን ለአገር ምስረታው እጅግ አስፈላጊነት አምነው በሕገመንግሥታቸው ውስጥ አስቀመጡት። ይህን ያደረጉበት ምክንያት ሕዝቡ በመጠኑ ልክ በመንግሥት ስልጣን ውስጥ ተገቢውን ውክልና እንዲያገኝ ነው። የአገሩ ባለቤት ህዝቡ ነውና በተመጣጠነ ውክልና አገሩን እንዲያስተዳድር ነው። በዚህ ቁጥር መሠረት የአገር ጥሪት እንዲከፋፈል ለማድረግ ነው። በእርግጥ የመብት ዕድገት ተጉዞ ተጉዞ ጫፍ ደርሶ “የግለሰብን ሚስጥር ለመበርበር ይረዳል” በሚል ምክንያት የሕዝብ ቆጠራን የሚቃወሙ ወገኖች መነሳታቸው ይሰማል።

የአሜሪካ ዴሞክራሢ የማዕዘን ድንጋይ ሰዎች እኩል ይወለዳሉ ይላል። እንደ ሕይወት ሩጫቸው ፍጥነትና ዝግመት የመበላለጥ መብታቸውን ላለመገደብ የተጠነቀቀ ይመስላል። ለነገሩ የኢትዮጵያም ሕገመንግሥት “ሰዎች በሕግ ፊት እኩል ናቸው።” ይላል።

በኢትዮጵያ ሕጉ ይህን ይበል እንጂ በተግባር የምናየው በቃልም የምንሰማው ከድንጋይ ዘመን ትውልድ እንጂ ዘመናችንን የዋጀ አይደለም። “እናንተ ወርቅ ሕዝቦች….” ብሎ መለስ በሕግ ሊያስቀጣ የሚገባ ሕገመንግሥቱን የሚፃረር ንግግር አደረገ። ያለመብሰል ነው ብለን ተውነው። አባይ ፀሀዬ መቁዋሚያ በመያዥያው እድሜ “እንዴት ጤነኛ ዐዕምሮ ልማት  በሕዝብ ቁጥር ልክ ይታደል ብሎ ይጠይቃል?” ብሎ ተደነቀ። “አጀብ!” አለ። ከዛም አልፎ ይህ የሚሆነው በኢህአደግ መቃብር ላይ ነው ብሎ ፎለለ። ህወሀት ጋ የኢትዮጵያ ሕዝብ በአራት አቢይ ክፍሎች ይከፈላል። ወርቅ፥ ትምክህተኛ፥ ጠባብና ሌሎች። ልማት ሲስፋፋም ቀመሩ ይሄ ነው። ይሄን መቀበል ከሰውነት መውረድ ነውና የኢሕአደግ አባል ድርጅቶች የአባይን ጥያቄ ተቀብላችሁ ለፍትሀዊ የልማት ስርጭት ስትሉ የኢህአደግን መቃብር ቆፍሩ።

ኦህዲዶች ከንደዚህ ዓይነት ሰዎች ጋር ሥትሠሩ መቆየታችሁ የሚደንቅ ነው። መጪው ጊዜም ምን ያህል ከባድና አደገኛ እንደሆነ ይታያል። ሠላሣ ዐመታትን በከተማ ውስጥ መኖር ጥጋቡ ተጨምሮ የባሰ አደነቆራቸው እንጂ የሰናፍጭ ቅንጣት ታህል ሥልጣኔ አልገባቸውም። ህወሀት አሁንም ጅራታም ነው። መብት በተጠየቀ ቁጥር ሊናከስ ጅራቱን ይነሰንሳል። ህወሀት ዛሬም ጥፍራም ነው። ዜጎች ይህን ሁሉ ሕዝብ ለያዘ አካባቢ አንድ ሆስፒታል ይገባናል ብለው ሲጠይቁ ተቀምጦ ከመነጋገር ይልቅ ሊቡዋጭር ጥፍሩን ያሾላል። ህወሀት ከበረሀ ከወጣ ሠላሣ ዘመን ሊደፍን ተቃርቦም ቀንዳም ነው። አካባቢያችንን እራሣችን እናስተዳድር ሲሉት ሊዋጋ ቀንዱን ያሾላል። ህወሀት እያንዳንዳችሁን ሊበላችሁ ቀን እየጠበቀ መሆኑን ማወቅ ቀላል ነው። ሳያጠፋችሁ ቅደሙት። ኢሕአደግን አፍርሱና ብቻውን አስቀሩት። ያም ቢቀር በምትወክሉት ሕዝብ ቁጥር የኢህአደግ መቀመጫ የሚከፋፈልበት ቀመር አውጡ። ይሄ እነሱን ሊያማቸው ይችላል ለኛ ግን ፍትህ ነው። አለዛ የምትወክሉት ሕዝብ ይሸማቀቅባችሁዋል። ሕዝብ ከጎናችሁ ነውና ተነሱ። ሰው ሆኖ ተፈጥሮ ከሰው ማነስን መቀበል ሕዝብን ብቻ ሳይሆን እኩል አርጎ የሠራንን ፈጣሪንም ማሳዘን ነው።

ሰው ከትምህርት ቤት ብቻ አይደለም ትምህርት የሚቀስመው – ተዕለት ዕለት የኑሮ ተራክቦውም እንጂ። እስከ ምክትል ጠቅላይ ሚኒሥትር ደረጃ የደረሠ፥ ለሠላሣ ዓመታት ከተማ ውስጥ የኖረ በውነት ይህን ንግግር ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል? ከህወሀት ጋር በንግግር ለመግባባት የምታስቡ ወገኖች ከምን ዓይነት ሰዎች ጋር እንደምትቀመጡ አስቡበት። ብስለታቸው ከቀን ወደ ቀን በብርሃን ፍጥነት እንደግመል ሽንት ወደሁዋላ እየተምዘገዘገ ነው። ውሀ ቢወቅጡት እንቦጭ።

Share this post

One thought on “የዕውቀት ፀሀይ ሳትወጣ የጠለቀችበት አባይ ፀሀዬ (በድንበሩ ደግነቱ)

  1. Abay is stupid. OutWe have a constitution that allows regions to cede whenever they want. What Abay and the TPLF people want is to put every factory, every university, every other infrastructure in Tigray. What is our guarantee that things built in Tigray belong itto other Ethiopians too? Because the Constitution says one economic society? I know what you are trying to suggest – federal investments based on economic feasibility or helping out less resourceful regions by putting factories, etc. Thanks but no thanks. Fool your mother. We know with home we are dealing. We want our fair share. The politics in Ethiopia is not geared to create one economic society. There is no labour mobility because of bad politics. Even if it is done like that, there is no guarantee when we see a million people being displaced in a week. Abhay, no one buys your stupidity.

    Reply

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.