የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል መስከረም 23 እና 24 ተከብሮ ይውላል- አባ ገዳዎች

የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል መስከረም 23 እና 24 ተከብሮ ይውላል- አባ ገዳዎች

አዲስ አበባ፡ መስከረም 6 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል መስከረም 23 እና 24 ተከብሮ እንደሚውል አባገዳዎች ዛሬ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

በዚህም የሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል መስከረም 23 በአዲስ አበባ ፣ የሆራ አርሰዲ ኢሬቻ በዓል ደግሞ መስከረም 24 ቀን 2013 ዓ.ም በቢሾፍቱ እንደሚከበር አባገዳዎቹ ገልጸዋል፡፡

አባ ገዳዎቹ የኢሬቻ በዓል በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች በሚታደሙበት ሲከበር መቆየቱን አስታውሰው ÷ የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል ግን የኮቪድ -19 ወረርሽኝን ከግምት ባስገባ መልኩ እንደሚከበርም ነው የገለጹት።

በኢሬቻ በዓል ላይ የሚሳተፉ ሰዎች ቁጥር በሽታውን ለመከላከል እና የጤና ባለሙያዎች በሚሰጡት ምክር መሰረት የሚወሰን መሆኑ ተገልጿል።

አባገዳዎቹ አያይዘውም የገዳ ስርዓት ባለቤት የሆነው የኦሮሞ ህዝብም ይህንን ከግምት በማስገባት በዓሉን እንዲያከብር ጥሪ ማቅረባቸውን ከኦሮሚያ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያኘነው መረጃ ያመላክታል።

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

The post የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል መስከረም 23 እና 24 ተከብሮ ይውላል- አባ ገዳዎች appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply