የዚምባቡዌው ፕሬዚዳንት የቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክን ጎበኙ

Source: https://fanabc.com/2019/02/%E1%8B%A8%E1%8B%9A%E1%88%9D%E1%89%A3%E1%89%A1%E1%8B%8C%E1%8B%8D-%E1%8D%95%E1%88%AC%E1%8B%9A%E1%8B%B3%E1%8A%95%E1%89%B5-%E1%8B%A8%E1%89%A6%E1%88%8C-%E1%88%88%E1%88%9A-%E1%8A%A2%E1%8A%95%E1%8B%B1/

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 4 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) የዚምባቡዌው ፕሬዚዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ የቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪያል ፓርክን ጎበኙ።

ፕሬዚዳንቱ በጉብኝታቸው ወቅት ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ ለመሸጋጋር እያደረገች ያለውን ከፍተኛ እንቅስቃሴ አድንቀዋል።

ሃገራቸውም በዘርፉ ከኢትዮጵያ በርካታ ልምዶችን መቅሰም ትችላለችም ነው ያሉት።

አሁን ላይ በኢትዮጵያ እየተገነቡ ያሉ የኢንዱስትሪ ፓርኮች የስራ እድል በመፍጠር በኩል ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረጉ መሆኑንም ተናግረዋል።

 

 

መረጃው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ነው፤

 

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.