የደሕንነት ተቋሙ ኋላፊነትና ተጠያቂነት ከምን ድረስ ነው ???

Source: https://mereja.com/amharic/v2/170110

የደሕንነት ተቋሙ ኋላፊነትና ተጠያቂነት ከምን ድረስ ነው ???
የደሕንነት መስሪያ ቤቱ ከወንጀለኞች በላይ ትልቅ ወንጀለኛ ነው። የአንድን አገር ደሕንነትና ሰላም እንዲሁም የጠንካራ መንግስትነትን የውስጥ ጉዳዮች በአስተማማኝነት ላይ ተመስርቶ የሃገርና ሕዝብ ሕልውና እንዲከበር ትልቁን ስራ መስራት ያለበት የደሕንነት ቢሮው ነው።
ካሁን ቀደም በተደጋጋሚ እንደተገለጸው የደሕንነት ተቋሙ ስራ የተዝረከረከ ነው። ይህንን መንግስት የማስተካከል ኃላፊነት ነበረበት አለበት ከሰኔው 16 የቦምብ ፍንዳታ ጀምሮ እስከ ዛሬው የብጥብጥና ሁከት ሂደት ውስጥ ደሕንነት ቢሮው ቅድሚያ መከላከል ሲያደርግም ሆነ ምንም አይነት የማክሸፍ ስራዎችን ሲሰራ አልታየም።

ቦምብ ሲፈነዳ፣ መፈንቅለ መንግስት ያሉት ሲሰናዳ፣ ከተሞች በነውጠኞች ሲደበላልቁ፣ ቤተክርስቲያናትና መስጂዶች ሲቃተሉ፣ ዜጎች በአደባባይ ሲታረዱ ሲገደሉ፣ የሐገር ሐብት ሲወድም፣ ዩንቨርስቲዎች በጸጉረ ልውጥ አሸባሪዎች ስወረር፣ ወዘተ የደሕንነት ተቋሙ የመረጃ ሰዎች ምን እየሰሩ ነበር ?
የደሕንነት ተቋሙ ስራ ምንድን ነው ? የዜጎችን ሰላምና ደሕንነት መጠበቅ ካልቻለ ፈርሶ ድጋሚ በጠንካራ መዋቅር ሊደራጅ ይገባል። በሃገሪቱ ለሚከሰቱና ለተከሰቱ ችግሮች በቅድሚያ መጠየቅ ያለበት ከወንጀለኞቹም በላይ ኃላፊነት መውሰድ ያለበት የደሕንነት ተቋሙ ነው። #MinilikSalsawi

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.