የደኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ መግለጫ ለክልል እንዋቀር ጠያቂዎች ግልጽ አይደለም ተባለ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/131436
https://radiodownloaddw-a.akamaihd.net/Events/dwelle/dira/mp3/amh/6621D674_2_dwdownload.mp3

የመንግስትን እውቅና እንደሚሹ ተናግረዋል። የደኢህዴን መግለጫ በተለይ ለሲዳማ ተወላጅ ምሁራን ስላልተዋጠላቸው በራሳቸው ወጣቶችን እና የሃገር ሽማግሌዎችን አስተባብረው በይፋ ክልልነታቸውን ሲያውጁ የመንግስት ባለስልጣናት አንዳቸውም አልተገኙም።
ከደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) ማዕከላዊ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ
ድርጅታችን ደኢህዴን ባለፉት 28 ዓመታት የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦችን አስተባብሮ በመምራት በክልሉ ዉስጥ የልማት፤ የሰላም፤ የዴሞክራሲ ድሎችን አስመዝግቧል፡፡ በሀገራችን ከሚገኙ ብሔሮች ብሔረሰቦች 70 በመቶዉ ይዞ የተደራጀ ነዉ፡፡ የደቡብ ብሔሮች፤ ብሔረሰቦችና፤ ህዝቦች ክልል ህዝቦችን በህብረ-ብሔራዊ አንድነት እየመራ የሚገኝ ዲሞክራሲያዊና ህዝባዊ ድርጅት ነው፡፡ ይህም ክልላችን የብዝሀነት ማዕከል፤ የአብሮነትና የአንድነት ማሳያ እንዲሆን አድርጓል፡፡
ደኢህዴን ለህዝቦች እንድነትና ለሀገር ግንባታ ግንባር ቀደም ሚናዉን የተወጣና እየተወጣ የሚገኝ ድርጅት ሲሆን ሀገራችን የገጠማትን ተግዳሮቶች ለመፍታት መፍትሄ የሚሆኑ ዉሳኔዎችን ያስተላለፈና ስኬቶችን ያስመዘገበ ድርጅት እንደሆነም ገምግሟል፡፡ በሀገራችን ያጋጠሙ ችግሮችን ለማለፍ በተደረጉ ትግሎች ከእህት ድርጅቶች ጋር በመሆን የራሱን ጉልህ ሚና የተወጣ ድርጅት ነዉ፡፡ በሀገራችን ኢትዮጵያ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ያገጠሙ ችግሮችን ለመፍታት በተደረጉ ትግሎች ሠላማዊ የስልጣን ሸግግር ለማድረግ ታሪካዊ ኃላፊነት ተወጥቷል፡፡ ስለሆነም ድርጅታችን ሀገራዊ ለዉጡ እዉን እንዲሆን ግንባር ቀደም ሚና የተወጣና ታሪካዊ ዉሳኔ ያስተላለፈ ድርጅት እንደመሆኑ ለቀጣይነቱም ግንባር ቀደም ሚናዉን እንዲወጣ ማዕካላዊ ኮሚቴዉ አጽንዖት ሰጥቷል፡፡
የደኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ላለፉት 10 ተከታታይ ቀናት ባካሄደዉ ስብሰባ ሀገራዊ የስላምና ፀጥታ ሁኔታን ከአህጉራዊና አለም አቀፋዊ ሁኔታ ጋር በማገናዘብ ገምግሟል፡፡
አሁን ሀገራችን ያለችበት ሁኔታም በዝርዝር አይቷል፡፡ ሁኔታዉን ለመቀየር ሁሉንም ህዝቦች በማረባረብ ሠላማችንን ማስከበር

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.